ኢትዮጲያን መልሶ የቀይ ባሕር ሀይል የሚያደርግ ፖሊሲ ያስፈልጋል ~ ጻድቃን ገብረትንሳኤ [+Audio]
በስራ
ላይ ያለው የብሔራዊ ደህንነትና የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ በቀይ ባህር ላይ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ለኢትዮጲያ ያላቸውን
አንድምታ ታሳቢ ያላደረገ እና ችግር ያለበት ነው በማለት ሌተናንት ጄኔራል ጻድቃን ገብረትንሣኤ ተቹ።
የቀድሞው
የሀገር መከላከያ ኤታማጆር ሹም ጻድቃን ገብረትንሣኤ ይህን የተናገሩት ከመንግስታዊው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር በቅርቡ
ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ነው። ጋዜጣው የጻድቃንን አስተያየቶች በከፊል ያላቀረባቸው ቢሆንም፤ ሆርን አፌይርስ ሙሉ
የድምጽ ቅጂው ደርሶታል።
ጄኔራል ጻድቃን
‹‹ኢትዮጲያ ትልቅ ሀገር ነው። በቀይ ባህር የሚደረገው ሁሉ ያሳስበናል። እኛ የቀይ ባህር ሀገር ነን። ከቀይባህር
የተነጠልን እንድንሆን መፍቀድ የለብንም።….በኤርትራ ሳቢነት ሆነ በራሳቸው በቀይ ባህር አካባቢ የሚንቀሳቀሱ
የተለያዩ ሀይሎች አሉ። ቀይ ባህር እኛን እና የባህረ ሰላጤው ሀገራትን የሚለይ ባህር ነው። ከፍተኛ የንግድ
እንቅስቃሴ የሚደረግበት ነው። የኛ የብሔራዊ ደህንነትና የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ በዚህ ረገድ ውጤታማ ነው ብዬ አላስብም።
እንደገና መታየት ያለበት ትልቅ ነገር አለ›› ሲሉ አሳስበዋል፡፡
ኢትዮጲያን
መልሶ የቀይ ባህር ሀይል ማድረግ የፖሊሲው ግብ ሊሆን እንደሚገባ የጠቆሙት ጻድቃን፤ ‹‹ይህ ማለት የግድ ወሮ
በመያዝ ላይሆን ይችላል….ካለን የሕዝብ ብዛት፣ ለባህሩ ካለን ቅርበት፣ ከኢኮኖሚያችን እድገት አንጻር፤ ሌሎች
ለዝንተ-ዓለም ቀይ ባህር የማንጠጋበት ሁኔታ እየፈጠሩ ባሉበት ሁኔታ ዝም ብለን ማየት የለብንም›› ብለዋል።
‹‹ይሄ ለአሁኑ
ብቻ ሳይሆን ለወደፊቱም ለመንቀል አስቸጋሪ የሆነ ነቀርሳ እየተተከለ ያለ ነው የሚመስለኝ›› በማለት፤ ከዚህ
አንጻር ነባሩ ፖሊሲ ‹‹ትልቅ ችግር ያለበት ነው›› በማለት አጽንኦት ሰጥተዋል።
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ