2017 ጁን 18, እሑድ

የትግራይ ሕዝብ ትናንት ታግዬ አታግዬ ለወገኖቼም ድጋፍ ሰጥቼ የተለየ ጥቅም ይገባኛል አላለም

https://www.facebook.com/TG Onorham

********* amazing-speech **********

የትግራይ ሕዝብ ትናንት ታግዬ አታግዬ ለወገኖቼም ድጋፍ ሰጥቼ የተለየ ጥቅም ይገባኛል አላለም

የትግራይ ሕዝብ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርገዋል ይሁን እንጂ ከፍተኛ ጥቅም ይገባኛል አላለም።

ሰሞኑን ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ከተለያዩ የመንግስት እና የፓርቲ የስራ ሃላፊዎች ጋር በወቅታዊ ሁኔታዎች ዙሪ ያ ውይይት አካሂዶ ነበር .. በውይይት ተካፋይ ከነበሩት አንዱ የሆኑት የት\ት ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ጸረ ህዝብ ሃይሎች አለ ስለሚሉት እና ለፕሮፖጋንዳ ግብአትነት እያዋሉ ሰለሚገኙት የህወሃት የበላይነት በተመለከተ ለተጠየቁት ጥያቄ የሰጡትን ምላሽ ..ቃል በቃል ወደጽሁፍ ቀይረን እንዲህ አቅርበነዋል 
...................................................................
« ሃገሪቱ ምን ታመነጫለች ለማን ምን እንስጥ ተብሎ በፍትሃዊ በሆነ ቀመር እንደሚሰራ አውቃለሁ ህያው ምስክር ነኝ ስለዚህ በዚህ በኩልም በመንግስት ስልጣን የማንንም ብሄር የበላይነት የሚያሳይ ምንም ነገር የለም 
እነሱ በስም የሚያነሱት የትግራይ ህዝብም ሆነ ህወሃትን ወስደን በምንመለከትበት ጊዜ በህገ መንግስቱም ሆነ በፓርቲ አስራራችን ውስጥ ህወሃት የበላይነት የለውም የህወሃትን የበላይነት ወይንም በኢትዮጵያ ህገመንግስት ውስጥ የትግራይን ህዝብ የበላይነት የሚያሳይ ምንም ነገር የለም እንደማንኛውም ህዝቦችና ድርጀት የራሳቸው ተገቢና አስፈላጊ ስፍራ አላቸው ታድያ ይህ ከሆነ ለምንድነው እነዚህ የትምክህትና የጥበት ሃይሎች የበላይነት ያለ አስመስለው የሚስሉት እና የሚጠሉት ተብሎ ሲታይ ሁለት ነገር በደንብ መታየት አለበት አንደኛ አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ የመጣውን ለውጥ በመምራት እና በማስተባበር መነሻ የነበረው ህወሃት ነው ህወሃትንም ያፈለቀው የትግራይ ህዝብ ነው ትግሉ በተደረጀና በተቀናጀ መንገድ በአንድ አላማ ዙሪያ እንዲካሄድ የተደረገበት ቦታ ቢኖር የትግራይ ህዝቦች ናቸው ለዚህ አስተዋጽኦ ያደረጉት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ታጋዮች የህይወትና የአካል መስዋት አድርገዋል ከፍለዋል እነዚህ ታጋዮች በዚህ አካባቢ ይህን ለውጥ የሚያመጣ አላማ ሲቀርጹና ለለሎች የሃገራችን ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች አብዮታውያን ሃይሎች ሃሳባቸውን ሲያጋሩ አቅፈው ደግፈው ይዘው ልጆቻቸውን አዋተው ደም ከፍለው ህይወት ገብረው ትግሉን አስቀጥለዋል ህወሃትም ሌሎች የጸረ ጭቆና ሃይሎችን በማስተባበር ትልቅ ኢትዮጵያዊ ማእበል እንዲፈጠር ደርግን የመሰለ ትልቅ የተደረጀ ሃይል ያለው መንግስት እንዲደመሰስ አድርጏል.. ይህን ሲያደርግ ደግሞ ግብታዊ በሆነ ሁኔታ ሳይሆን ረጂም እቅድ ነድፎ ከድል በሁዋላ ሊኖር ስለሚችለው ልማት .. ሊኖር ስለሚገባው ሰላም ትበተናለች የተባለችውን ሃገር ደሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ እንደት የሃገሪቱ ብሀር ብህረሰቦች እና ህዝቦች እኩል የሉአላዊ የስልጣን ባለቤት እንዲሆኑ እኩል በተመጣጣኝ ውክልና የስልጣን ባለቤት እንዲሆኑ የሚያስችል ሃሳብ በማመንጨትና በማሳተፍ አደራጅⶆል አታግⶀል ስለዚህ ትምክተኞች የሚጠሉት ለዘላለም እንዳይመለሱ አድርጎ ከስራቸው እንዲመነገሉና ሃሳባቸው የጥፋት እንደሆነ የሃገራችን ህዝቦች እንዲያውቁ ስላደረገ በዚህም ዙሪያ የነሱ ጥፋት ላይ ያታገለ ድርጅት ስለሆነ ይጠሉታል የትግራይም ህዝብ የዚህ ድርጅት ምንጭ ስለሆነ ይጠሉታል ጠባቦች ለዘመናት በህዝቦች ስም እየነገዱ በተጨባጭ ግን ለህዝቡ ሰላም ልማት ዲሞክራሲ እኩልነት አብዮታዊ ሃይሎች ከነዚህ ከተበደሉት ህዝቦች ሃሳቡን በማመንጨት እና እኩል በማታገል እነዚህ ሃይሎች ገዥ ሆነው እንዳይቀመጡ ያደረገ ስለሆነ ይጠሉታል ለህዝቡ ታድያ የበላይነት ያለ ለማስመሰል ፣ምንድነው ተስሎ የሚቀርበው የሚለውን በሁለተኛ ደረጃ ማየት ያስፈልጋል ዛሬም ቢሆን የትግራይ ህዝብ ትናንት ታግዬ አታግዬ ለወገኖቼም ድጋፍ ሰጥቼ ለውጥ በማምጣቴ የተለየ ጥቅም ይገባኛል አላለም እንደማንኛውም የኢትዮጵያ ህዝብ ይልቁንም ተራሮችን እና ድንጋይ ዛሬም ትልቅ የተፈትሮ ሃብት ስራ እየሰራ ውሃ እያመነጨ ከድህነት ጋር አዲስ ትግል የገጠመ ህይወቱን በዚህ መሰረት ላይ ጥሎ እየሰራ ያለ ህዝብ ነው ህወሃት እንደ ድርጅትም በዚሁ መንገድ በሚያስተዳድርበት ክልል የህዝቡን አቅም አስተባብሮ ልማት እንዲመጣ ሰላም እንዲሰፍን ዲሞክራሲያዊ መብት እንዲረጋገጥ ለኢትዮጵያም ህዝቦች ከድህነት እና ከጉስቁልና እንዲወጡ ለማድረግ አመራር በመስጠት ላይ ያለ ድርጅት ነው በሃገር አቀፍ ደረጃም በሚሰጠው አመራር የጋራ ድርሻውን በተዋጽኦው ልክ እያበረከተ የሃገራችን ህዝቦ እነዚህን ቅድም ያልኩዋቸውን የሰላም የልማት የዲሞክራሲያዊ አስተዋጽ ኦዎች እንዲያድጉ እያደረገ ያለ ድርጅት ነው ይህ መሆኑ ሳይጠፋቸው ይህን እውነት ሳያጡት ጥቂት በህወሃትና በትግራይ ህዝብ ስም የሚነግዱ ሰዎች የትኛውም ብሄር ውስጥ እንዳሉ ጥገኞች ትግራይ ውስጥም አሉ........... የትኛውም ብሄር ውስጥ እንዳለ አመራር ብልሽት ህወሃትም ውስጥም አለ ... ይህን የአመራር ብቻ ነቅሶ በማውጣት የትግራይ የበላይነት ያለ በማስመሰል ቅድም ባልኰዋቸው ሁኔታዎች መንግስት ማቅረብ በነበረብን የልማት በ አግባቡ ያልተጠቀሙ የህብረተሰብ ክፍሎችን ልብ በሚኮረኩር መንገድ ሌሎች ህዝቦች መልማት ያልቻሉትና በአግባቡ ያልተጠቀሙት ድርሻቸውን ህወሃት ሰለወሰደው ነው ድርሻችሁን የትግራይ ህዝብ ወስዶት ነው ብሎ ወደተሳሳተ ታርጌት እንዲተኩስ .....ትክክለኛ በሽታ መጀመሪያ የራስን አመራር ማጥራት ቀጥሎ በራስ አቅም ያሉ ልማት ማልማት ለሁሉ ፍትሃዊ ልማት ማምጣት ..... በትግራይ ህዝብ ስም እና በ ህወሃት ውስጥ ያለ ብልሽትም ካለ ደህዴን ውስጥ እንዳለ ኦህዲድ ውስጥ እንዳለ ብአዴን ውስጥ እንዳለ እንዳይታገሉ ወደዚህ ቦታ ወሰተሳሳተ ታርገጥ እንዲተኩሱ በማድረግ የሚሰሩበት ምክንያት ሃይል ለማሰባሰብ አስበው ነው እና ዋናው ከስር ከመሰረታቸው እንዲነቀሉ ስላደረገ የመነሻ ትግሉ ጠንሳሽ እሱ ስለሆነ እሱን ከመታህ ተመልሰህ ያንን ያጣሀውን ቦታ ለመያዝ ትችላለህ ከሚል የተሳሳተ ግምት ነው ስለዚህ ይህ መጀመሪያውኑም ቢሆን ይህ ለውጥ እና ትግል በምኞትና ዝም ብሎ በቀላል መስዋትነት የመጣ አይደለም ከፍተኛ ዋጋ የተከፈለበት ከፍተኛ ትግል የተደረገበት የህዝቦች መስዋእትነት የተከፈለበት ትግል ነው ስለዚህ አሁንም መጀመሪያ ወደ ውስጥ ማየት .. እንደ ኢህአዴግ እንደ ድርጅት ያሉበትን ችግሮች ማጽዳት ..እራሱ ከነዚህ ችግሮች መጀመሪያ ነጻ ከሆነ በሁዋላ የዚህ ችግር አስተሳሰብ ለመስረጽ የሞከሩባቸው ቦታዎችን የነሱ ነጻ መሬትና ነጻ ወረዳ እንዳይደለ እንዲገነዘቡ ማድረግና ወደልባችን ተመልሰን በመንግስት እና በድርጅት ውስጥ ያለ ብልሽት እና የመልካም አስተዳደር ችግርን በማረም የህዝቦች ተቃሚነትን በማረጋገጥ የወጣቱን ተጠቃሚነት በፍጥነት ምላሽ በመስጠት ወጣቱም በሃገር ግንባተ ውስጥ የራሱን አስተዋጽ እንዲያደርግ በማስቻል እነዚህን ከንቱ ተስፈኞች ተስፋቸው ከንቱ እንደሆነ ማሳወቅ ይገባል »
በጋዜጠኛ ተክለሃይማኖት ገብረመድህን 
መቀሌ 

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ