2017 ማርች 5, እሑድ

የትግራይ ህዝብ የለውጡ ኣጋር እንጂ ተጠቂ ሊሆንኣይገባም kkkkkkkkk

tg onorham
የትግራይ ህዝብ

የለውጡ ኣጋር እንጂ
ተጠቂ ሊሆንኣይገባም

መርስዔ ኪዳን

ሜኔሶታ፤ ሃገረ ኣሜሪካ
ሰሞኑን በሃገራችን ውስጥ እየተካሄደ ባለው ህዝባዊ
አመፅ ምክኒያት ብዙ የሰው ህይወት፣
የኣካል ጉዳትና የንብረት
ውድመት እየደረሰ ነው። ይህ ሁኔታ
እንዲፈጠር ያበቁ ብዙ ምክኒያቶች
ቢኖሩትም ኣንዱና ዋነኛው ምክኒያት
በሃገሪቱ
ውስጥ ፍትሃዊ የሆነ የፖለቲካ ስርዓት
ኣለመኖሩ ነው። ኢትዮጵያ ብዙ
ብሄሮች ብቻ ሳይሆን ብዙ ፖለቲካዊ
ማህበራዊና
ኢኮኖሚያዊ አመለካከት ያለው
ህዝብ የሚኖርባት አገር ነች። ሆኖም
ያለው የፖለቲካ ስርአትና በስልጣን
ላይ ያለው
መንግስት ይህንን ልዩነት ማክበርና
ማስተናገድ ባለመቻሉ ብቻ ሳይሆን
ፍላጎትም ባለማሳየቱ ለዚህ ችግር
ተዳርገናል።ኢህኣዴግ የሚመራው
መንግስት ሠሞኑን የተፈጠረውንችግር በተመለክተ ያወጣው
መግለጫ የችግሩን መጠን በውሉ
ያላጤነና ጭራሽም ዋነኛውን የችግሮቹ ሁሉ መንስኤ ያልተመለከተ ነው። 1
ለሙስናውም፣ ለመልካም አስተዳደር እጦቱም፡
ለብሄር ነክ ጥያቄዎችም፤ ለሌሎች ችግሮችም ምክኒያት የሆኑት ዋነኞቹ መሰረታዊ
ችግሮች ህዝብ ያሻውን የሚመርጥበት
ዴሞክራሲያዊ ስርኣት አለመኖር፣ ህዝብ ሲበደል ብሶቱን የሚገልፅበት ነፃ መድረክአለመኖር፣ የተለየዩ የፖለቲካ
አመለካከቶች የተወከሉበት መንግስት አለመኖር፣ የኣገሪቱ ህግ አውጪና ህግ ኣስፈፃሚ
ኣካላት መቶ በመቶ በኢህኣዴግ
ቁጥጥር ስር መሆን፣ የፍትህ ኣካላት በነፃነት ለመስራት አለመቻል ናቸው።
ሰሞኑን በኦሮሞና በአማራ ክልሎች የተነሱት ተቃውሞዎች መነሾዎች የተለያዩ ይሁኑ
እንጂ ዋነኛው ምክኒያት ከላይ
የዘረዘርኳቸው መሰረታዊ ችግሮች ውስጥ ውስጡን ሲብላሉ ቆይተው በመፈንዳታቸው
ነው። የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ ነገሮች
ካልተስተካከሉ የትግራይም ሆነ የሌላው ክልል ህዝብ መነሳቱ አይቀርም። እነዚህ ችግሮች
ከብሄር ብሄር ሳይለዩ ሁሉንም
ያማረሩ መሆናቸው የታወቀ ሆኖ ሳለ፤ አንዳንድ ፅንፈኛ አካላት ሁኔታውን አንዱ ብሄር
ተጠቃሚ አንዱ ብሄር ተጎጂ
እንደሆነ አድርገው በመቅረፅ ለኣገሪቷም ሆነ ለየትኛውም ህዝብ የማይበጅ፣ አንድ ብሄር
ላይ ያነጣጠረ ዘመቻ በማካሄድ
ላይ ይገኛሉ። በተለይም በኤርትራ መንግስት ባጀት ተበጅቶለት የሚንቀሳቀሰው ኢሳት
በግልፅ በትግሬዎች ላይ በታሪክና
በህግ ተጠያቂ የሚያደርግ አደገኛ ዘመቻ በማካሄድ ላይ ይገኛል። 2 እውነት ለኢትዮጵያ
ህዝብ ቀና የምንመኝ ሰዎች ይህንንድርጊት በጋራ ልናወግዘውና ልንቃወመው ይገባል። በዚህ አጭር ፅሁፍ ትግሬው በዚህ
መንግስት በተለየ ተጠቅሟል
የሚለው አመለካከት ትክክል እንዳልሆነ፣ በኦሮሞ፣ በኣማራና በሌሎችም ክልሎች ያሉ
በደሎች በትግራይም እንዳሉ
እንደውም የበለጠ አሳሳቢ እንደሆኑ፣ ትግሬዎች በኢትዮጵያ ውስጥ መፈጠር ለሚገባው
ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ ስርኣትዋነኛ ባለድርሻና ተዋናይ መሆን እንደሚገባቸው፣ ይህን ለውጥ ለማምጣት የሚደረገው
ትግልም ሰላማዊና ሰላማዊ ብቻ
መሆን እንዳለበት ለማስገንዘብ እሞክራለሁ።
ትግሬው በዚህ መንግስት ከሌላው በተለየ ተጠቃሚ ሆኗልን?
ሕወሓት የበላይ የሆነበት የኢትዮጵያ ህዝቦች ኣብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህኣዴግ)
ስልጣን በያዘ ማግስት
አብዛኛውን ቁልፍ የፌደራል መንግስት ስልጣናት የሕወሓት አባላት እንደያዙ የታወቀ ነው።
በተለይ ደግሞ የመከላከያ
ሃይሉ ሙሉ ለሙሉ ሊባል በሚችል ሁኔታ በሕወሓት ሰራዊትና ወታደራዊ ኣመራር ስር
መውደቁ ይታወቃል። በጊዜው
አዲስ የተመሰረቱት ክልሎችም ከሕወሓት አማካሪ ተመድቦላቸው እንደነበር የሚታወስ
ነው። ይህ ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ
በመጠኑም ቢሆን እየተለወጠ የመጣ ቢሆንም ሙሉ በሙሉ ተስተካክሏል ማለት
አይቻልም። ታዲያ ባለፉት ሃያ አምስትአመታት የነዚህ የሕወሓት ባለስልጣናትን መብዛት የተመለከቱ የሌላ ብሄር
ተወላጆች
ትግሬ በተለየ ተጠቃሚ የሆነበት
ስርዓት የተፈጠረ እንዲመስላቸው ሆኗል። ሁኖም ትግሬው ከሌላው ብሄር በተለየ
ተጠቅሞ እንደሆነ ለመመርመር
መመልከት ያለብን እነኚህን ጥቂት ባለስልጣናት ሳይሆን ኣብዛኛው ትግሬ የሚኖርበትን
የትግራይን ክልል ነው።
የትግራይ ክልል ከሌሎች ክልሎች ጋር በኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ መስኩ
ሲወዳደር በተለየ ተጠቅሟል
የሚያስብል ሁኔታ አንድም የለም። እንደውም ህዝቡ ክልሉን ለማሳደግና ለማልማት
ከሚጥረው ጥረት አንፃር ሲታይ ያለው
መንግስት ኣጋዥ ሳይሆን ማነቆ እንደሆነበት ማየት ይቻላል። ለምሳሌ መላው የትግራይ
ህዝብ ክልሉን ለማልማት የትግራይ
ልማት ማህበርን ኣቋቁሞ የበኩሉን ድርሻ ለመወጣት ሲጥር ቆይቷል፤ ሆኖም ሕወሓትየልማት ማህበሩን በነፃ
እንዲንቀሳቀስሊፈቅድለት ስላልቻለ አብዛኛው የልማት ማህበሩ አባል ራሱን ለማግለል ተገዷል።
የትግራይ ልማት ማህበር
በመጀመሪያዎቹ አመታት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኣባላት ያሉት የክልሉ መንግስት
ከሚሰራው በላይ ትምህርት ቤቶችንና ጤናጣቢያዎችን የሚሰራ ማህበር ነበር። አሁን ግን
ከህዝቡ ባለቤትነት ወጥቶ በሕወሓት ቁጥጥር ስር በመውደቁ አብዛኛው
አባላቱ በየወረዳቸውና አውራጃቸው የየራሳቸውን የልማት ማህበራት በመፍጠር ትተውትወጥተዋል።
በትግራይ ክልል የሚኖረው ህዝብ የአካባቢውን በረሃማነት ለመለወጥ በዓመት ለሁለት
ወራት ነፃ የጉልበት አገልግሎት
የሚሰጥ ሲሆን ከክልሉ ውጪ የሚኖረው ህዝብ ደግሞ በየወረዳው ትምህርት ቤቶችንና
ጤና ኬላዎችን በመስራት ከፍተኛ
ርብርብ ያካሂዳል። ይህ ህዝቡ የሚሰራው ስራ ክልሉን በነዚህ መስኮች የተሻለ ውጤት
እንዲያስመዘግብ አስችሎታል። 3 ይህ
የህዝቡ ጥረት ባይኖርበት ኑሮ የክልሉ መንግስት ብቻ የሚሰራው ስራ ከሌሎች ክልሎች
ያነሰ ይሆን ነበር።
በኢንቨስትመንት
ደረጃ ክልሉ ገብቶ
ለመስራት ፍላጎት
ያለው ብዙ ህዝብ
ቢኖርም በክልሉ
ያለው የአስተዳደር
ብልሹነት
አላሰራ ስላላቸው
አብዛኞች
ነጋዴዎች
በአዲስኣበባ ወይም
ሌሎች ክልሎች
ሄደው
ለመስራት
ተገደዋል። በክልሉ የሚገኙ
የተፈጥሮ ሃብቶች ኤፈርት በመባል በሚታወቀው የሕወሓት የንግድ ድርጅት ስር ካልሆነ
በስተቀር ሌሎች የግል ነጋዴዎች
እንዲሰሩባቸው የሚጋብዝ ሁኔታ የለም። ኤፈርት የሚባለው የንግድ ድርጅት አትራፊ
የሆኑ የንግድ ዘርፎችን በሞኖፖል
በመያዝ ሌሎች ነጋዴዎችን ከጨዋታ ውጪ እንዲሆኑ የሚያደርግ ነው። የክልሉ ህዝብ
ድርጅቱ በስሙ የተቋቋመ ቢሆንም
አንድም ግዜ የአፈፃፀም ሪፖርት ተደርጎለት ኣያውቅም። የድርጅቱ ትርፋማነት አጠያያቂ
ባይሆንም ትርፉ ምን ላይ ዋለ?ትግራይን መልሶ ለማቋቋም ምን ተደረገ? ለሚለው ጥያቄ ምንም ምላሽ የለም። በዚህ
ድርጅት ስር የተመዘገቡት ንብረቶች
ለባለቤቱ ለትግራይ ህዝብ የሚሸጋገሩበትን መንገድ ብዙዎቻችን ብንጠቁምም ሕወሓት
ይህን ጥያቄ ለመመለስ ምንም
ፍላጎት አላሳየም። 4
በማህበራዊ መስኩ የየክልሎቹን የስራ አፈፃጸም ብቃት ማሳያ ይሆን ዘንድ አንድ ላይ
የተጀመሩትን የባህርዳር፣ የመቀሌና
የአዋሳ የስፖርት ስቴድየሞች እንመልከት። የመቀሌ ስቴዲየም ከባህርዳሩም ሆነ ከሁለቱም
በኋላ ከተጀመረው ከ አዋሳስቴዲየም እኩል እንኳ ሊጠናቀቅ አልቻለም። ሕወሓት በዓሉን ሊያከብር ሲል በለብ ለብ
ከተሰራ በኋላ ለመጨረስ ዞር
ብሎ እንኳን ያየው የለም። የመቀሌ ሕዝብ በንፁህ ውሃ እጥረት ሲሰቃይ ይኽው ስንትአመት አስቆጠረ? በጣም
የምንኮራባቸውን የነ ኣፄ ዮሃንስን፣ እነ ኣሉላ አባነጋን፣ የኣድዋ ድልን እና ሌሎች ታሪካዊ
እሴቶቻችንን ለመጠበቅና
ለመጪው ትውልድ ለማስተላለፍ የተነሱ ቀና ኢትዮጵያውያንን አላሰራ በማለት ህዝቡንአፍኖት ይገኛል። 5 ከላይ
የዘረዘርኳቸውን ሁኔታዎች በቅጡ የተረዳ ሰው ትግሬው ከሌላው ኢትዮጵያዊ ወገኑ
የበለጠ ተጠቅሟል ሊል አይገባውም።
ብዙዎች ታዲያ ይህ ሁሉ ችግር ካለበት ለምን ትግሬውም እንደሌላው አይቃወምም?
ብለው ይጠይቃሉ። በመጀመሪያ
ደረጃ ትግሬው አይቃወምም የሚለው ድፍን ድምዳሜ ትክክል አይደለም። ብዙ የትግራይ
ልሂቃንና ፖለቲከኖች ከሌሎች
ባልተናነሰ ሁኔታ መንግስት ላይ የሰላ ትችትና ተቃውሞ ያቀርባሉ ለዚህም የቀድሞ
የድርጅቱ አባል የነበሩት ጄ/ ል ፃድቃን
ገ/ ትንሳይ፣ ጄ/ ል ኣበበ ተክለሃይማኖት፣ ገብሩ ኣስራት፣ ስዬ ኣብረሃ, ኣስገደ ገ/ ስላሴ ከነሱም
በተጨማሪ እንደ ፕ/ ር ተኮላ
ሓጎስ፣ ኣብረሃ በላይ፣ ፕ/ ር መድሃኔ ታደሰ፣ አብረሃ ደስታ፣ ፕ/ ር ገብሩ ታረቀ፣ ዶ/ ር ሃይሉ
ኣርኣያ እና ሌሎችንም
እንደምሳሌ መዘርዘር ይቻላል። ከነዚህም ኣንዳንዶቹ ልክ እንደ ኣማራው፣ ኦሮሞውና
ሌላው ተቃዋሚ እስር እንግልትና
ስደት ደርሶባቸዋል። እነኚህ ግለሰቦች
ናቸው፣ አብዛኛው ትግሬ ግን ሕወሓትን
ሲቃወም ኣይታይም የሚለው ክርክር
የተወሰነ እውነታ ኣለው። ግን ደግሞ
ምክኒያታዊ ነው። በትጥቅ ትግሉ ወቅት
ልጁን፣ ወንድሙን፣ እህቱን፣ ጓደኛውን
ያላጣ
ትግሬ የለም። በ 17 ዓመቱ ትግል ከ 60 ሺሕ
በላይ ወጣቶችን ያጣው ህዝብ በትግሉ
ያገኘውን ኣንፃራዊ ሰላም እንዲህ በቀላሉ
ሊያጣው ኣይፈልግም። ሌሎች በቀላሉሕወሓትን ለመቃወም የሚነሳሱትን ያክል
ትግሬውም እንዲነሳ መጠበቅ ይከብዳል።
ነገር ግን በጊዜ ሂደት በስልጣን ላይ ያሉት
የሕወሓት መሪዎች ከ 60 ሺሕ በላይ
ወጣቶቹ የተሰዉበትን ዓላማ ዘንግተው
ስልጣናቸውን እንደርስት ሲንከባከቡሲመለከትና የህዝብ መብት ሲደፈጠጥ
ሲመለከት ወንድሞቼና እህቶቼ የሞቱለት
መብቴ ተረገጠ የሚል ከፍተኛ ቁጭትና
ሃዘን ውስጥ ገብቷል።ሌላው ትግሬዎች የኢህኣዴግን በደል ኣይቃወሙም የሚለው ኣስተያየት የሚፈጠረው
የትግራይን ህዝብና ሕወሓትን ለይቶ
ካለማየት ነው። የትግሬዎችን
ጥቅም የሚነካ ነገር ላይ
ኣለመስማማት እንደ ሕወሓት
ደጋፊነት የሚያስቆጥርበት
ሁኔታ
ተፈጥሯል። ኣንዳንድ ሰዎች
የትግሬ የበላይነት ኣለ ሲሉ፤
አይ ስህተት ነው ችግሩም
በደሉም ሁላችንም
የምንጋራው ነው
እንጂ ትግሬ በተለየ
የተጠቀመበት ሁኔታ የለም
ብለን የምንለውን ሰዎች ያለውን በደል
እንደማንቃወም ተደርጎ ይወሰዳል።
የሑመራ፣ ወልቃይትና ፀገደ አከላለል ጉዳይ ጥሩ ምሳሌ ይሆናል። አብዛኛው ትግሬበሑመራ፣ ቃፍታ፣ ወልቃይትና ፀገደ
ወረዳዎች የሚኖሩት ኢትዮጵያውያን ትግሬዎች መሆናቸውን ያውቃል። ስለሆነም ቋንቋን
መሰረት ያደረገ የፌደራል ስርዓት
ሲፈጠር እነኚህ ወረዳዎች በትግራይ ክልል ውስጥ መመደባቸው ተገቢ ነው ብሎ ያምናል።
ታዲያ ወልቃይት በአማራ ክልል
ስር ይሁን የሚል ተቃውሞ ሲነሳ አብሮ እንዲነሳ እንዴት ይጠበቃል። ወቅታዊ በመሆኑየወልቃይትን ጉዳይ በትንሹም
ቢሆን ዘርዘር አድርጎ ማየቱ ይበጃል።ባንድ በኩል የወልቃይት ህዝብ ትግሬ ሳይሆን ኣማራ
ነው ስለሆነም በኣማራ ክልል ውስጥ ይታቀፍ የሚል አቋም የያዙ
አሉ። ይህ አቋም
ከእውነታው ፍፁም
የራቀና በኢሳት
ተደጋግሞ ስለተነገረ
ኣብዛኛው ሰው
እውነት የመሰለው
አቋም ነው።
በ 1987 ዓ.ም.
የተደረገው ቆጠራ
የሚያሳየው በቦታው
የሚኖረው ህዝብ
በአመዛኙ ትግሬ
መሆኑን ነው።
ምዕራብ ትግራይ
ምንጭ 1987 ህዝብ
ቆጠራ 6
ትግሬ
ኣማራ
45532
14226
ፀገደ
870992734
ወልቃይት
87012
10382
ፀለምቲ
41999
3780
ቃፍታ ሑመራ
ይህን መረጃ
አንዳንዶች ቆጠራውየተካሄደው በ ኢህኣዴግ ግዜ ስለሆነ አንቀበለውም
ይላሉ። ሆኖም በኢህድሪ ወይም
ደርግ ግዜ የተሰሩ የብሄር ጥናቶችም የሚያመላክቱት በነኚህ ወረዳዎች የሚኖረው ህዝብ
በኣመዛኙ ትግሬ መሆኑን ነው። 7
ከዚህ በታች የምትመለከቱተ ካርታ በ 1971 ዓ.ም. የተዘጋጀ ሲሆን፣ እንደሚታየው
በጊዜው በሰሜን ጎንደር ማለትም ሑመራ፣
ወልቃይት፣ ፀገደና ፀለምቲ ውስጥ የሚኖረው የትግርኛ ተናጋሪው ብሄረሰብ እንደሆነ
ያሳያል። የትግራይ ህዝብ ለ 17
አመታት ባደረገው ትግልም
የወልቃይት ህዝብ ዋና
ተሳታፊ ከመሆኑም ባሻገር
ወልቃይት
የሕወሓት ደጀን የነበረ ቦታ
እንደነበር ይታወቃል። ይህ
ማለት በነኝህ ኣከራካሪ
ቦታዎች ኣማራው
ኣይኖርም ነበር
ማለት ኣይደለም።
ከቀድሞም ቢሆን
ሁለቱ ህዝብ ኣገው፣
ኩናማና ሌሎች
ብሄሮችንም ጨምሮ ኣብሮ ይኖር እንደነበረ ማወቅ
ይገባል። ነገር ግን ከላይ በኣሃዙ
ማየት እንደሚቻለው በደርግ ጊዜ የነበረው ካርታም እንደሚያሳየው በኣካባቢው የሚኖረው
ዋነኛ ብሄረሰብ ትግሬው ነው።
ይህን መረጃ የተመለከቱ ሰዎች ታዲያ ለምን ህዝቡ ኣማራ ነን ብሎ ጠየቀ? ይላሉ። ይሄም
ተደጋግሞ ስለተነገረ እውነት
የመሰለ ውሸት ነው። በርግጥ በጎንደር የሚኖሩ ጥቂቶቹ በትክክልም ከወልቃይት አካባቢየሆኑ አብዛኛው ግን
የዛው የጎንደር
አካባቢ ሰዎች
ወልቃይት አማራ
ነው ብለው ኮሚቴ
አቋቁመው
ተንቀሳቅሰዋል።
ሆኖም ግን
በወልቃይትም ሆነ
በሌሎቹ
አከራካሪ ቦታዎች
እንዲህ
አይነት ጥያቄ ከህዝቡ
አልተነሳም።
ኣብዛኛው ህዝብ
ኢሳት በወልቃይት
ህዝቡ
አማራ ነኝ ብሎ
ጠየቀ እያለ
በአርማጭሆ ወረዳ
የተካሄደውን ስብሰባ
ልክ
ወልቃይት ውስጥ
እንደተካሄደአደርጎ
በማቅረቡ የተሳሳተ
መረጃ
ሰለባ ሆኗል።ኣንዳንዶች ደግሞ በዘር የሚደረግ መከፋፈል ትክክል አይደለም ስለዚህ
በወልቃይት የሚኖሩት ትግሬም ሆኑ አማራ ወደ
አማራ ክልል መዛወር አለባቸው የሚል ኣቋም ያራምዳሉ። በርግጥ ብሄርን ወይም ቋንቋን
ብቻ ያደረገ ፌደራሊዝም
እንደማይበጅ ብዙው ትግሬም ጭምር የሚስማማበት ነው። ግን ያ ማለት ቀድሞ በአፄ
ሃይለስላሴም ሆነ በደርግ ግዜየነበሩት አከላለሎች
ትክክልና ፍትሃዊ ናቸው
ማለት አይደለም።
ጥያቄው ለምን በቋንቋይከፋፈላል ከሆነ ሰሜኑ
የቀድሞ
የጎንደር ክፍል በትግራይ
መካለሉን
የምንቃወመውን ያክል
ደቡቡ የጎንደር ክፍልም
በኣማራ ክልል
መወሰኑንም መቃወም
ይገባል። ግማሹ የቀድሞ
ትግራይ ክፍለሃገር ወደ
አፋር ክልል እንዲካለል
ተደርጓል። ይህ ወደ አፋር
እንዲካለል የተደረገው
ክፍል በጣም ሰፊና ብዙ
ማዕድናት የታደለ ነው።
ሆኖም አፋሮች
የሚኖሩበት ስለሆነበኣፋር ክልል ስር መሆኑ አከራካሪ
አልሆነም።
ጉዳዩን በጥልቀት ያልተረዱ ሰዎች ደግሞ ለምን በአከራካሪ ቦታዎች ሪፈረንደም
ኣይካሄድም ብለው ይጠይቃሉ። ሪፈረንደም
ቢካሄድ ውጤቱ ያለውን ሁኔታ ብዙም እንደማይቀይር ከላይ ካሳየሁት ስታቲስቲካዊ መረጃማየት ይቻላል። እንዲያም ሁኖ
ሪፈረንደም ሊካሄድ የሚችለው ህገመንግስቱ ላይ በተደነገገው መሠረት ነው። አንድ ወረዳ
ሪፈረንደም እንዲያካሂድ
የወረዳው ምክርቤት ሁለት ሶስተኛው ሪፈረንደም እንዲካሄድ መወሰን አለበት። አሁን
ባለው ሁኔታ ደግሞ የወረዳውን
ምክርቤት ሙሉ በሙሉ የተቆጣጠረው ሕወሓት ነው። ብዙዎች ከሚያስቡት
በተቃራኒው፤ ሕወሓት ከትግራይ ጥቅም
ይልቅ ለስልጣኑ የበለጠ ቀናኢ ነው። ኣገሪቱን ባህር ወደብ ኣልባ ያደረገበትን ሁኔታ፣ በኣስር
ሺዎች መስዋእት ከሆኑ በኋላ
የኣልጀርስ ስምምነትን የፈረመበት ሁኔታ እና ሌሎችንም ተግባሮቹን ስንመለከት ለስልጣኑ
ሲል የትግራይንም ሆነ
የኢትዮጵያን ህዝብ ጥቅም ኣሳልፎ ከመስጠት እንደማይመለስ እንረዳለን። በወልቃይትጉዳይም ቢሆን ስልጣኑን
ለማስጠበቅ ሲል ከትግራይ ህዝብ ጥቅም ውጪ በጉዳዩ ለመደራደር ዝግጅት ላይ እንዳለምልክቶች ይታያሉ።
በዚህ ግዜ ትግሬው በሁለት በኩል ከባድ ኣደጋ ተደቅኖበታል። ባንድ በኩል ስልጣን ላይ ያለው
መንግስት የሚያደርስበት
ጭቆና በሌላ በኩል በተቃዋሚው በኩል የተደበቁ ጥቂት ዘረኝነት ያለባቸው ሃይሎች
የሚሰነዝሩበት ጥቃት። ስለዚህ ትግሉ
በመንግስት የሚደርስበትን ጭቆና መቀልበስ ብቻ ሳይሆን፤ በጥቂት ዘረኖች የተቃጣበትን
ጥቃት መቋቋም ጭምር ነው።
የሌላው ብሄር ልሂቃንም ሆነ ህዝቡ ይህን ተረድተው ከትግሬው ጎን በመቆም ከኣክራሪዎች
የሚደርስበትን ጥቃት በጋራ
ሊታገሉት ይገባል።
ለመላው ኢትዮጵያውያን መቅረብ ያለበት ጥያቄ ትግሉ የትግራይን ህዝብ ለመጉዳት ነው?ወይስ የሁሉም ጥቅም
የተከበረበት
ዴሞክራሲያዊና
ፍትሓዊ ስርዓት
ለመመስረት ነው?
ኣብዛኛው ቀና
ኢትዮጵያዊ የሁሉም
ጥቅም የሚከበርበት
ዴሞክራሲያዊና
ፍትሓዊ ስርዓት
ለመመስረት እንጂ
አንዱ ብሄር ላይ
የተለየ ጉዳት
እንዲደርስ ፍላጎት
እንደሌለው ኣከራካሪ
ኣይሆንም። የሁሉም
ባለድርሻ ጥቅም
የተጠበቀበት ስርዓት
ለመመስረት፤ ሁሉም
ባለድርሻ
የሚሳተፍበት ሂደት
ሊኖር
ይገባል እንጂ አንዱ
ተጠቅቶ ሰላማዊ ስርዓት ይፈጠራል ማለት ዘበት ነው።
ስለሆነም የሚከተሉት ባለድርሻዎች የሚከተሉትን ተግባሮች ሊፈፅሙ ይገባል
የትግራይ ህዝብ እስካሁን በጎንደር በተደረገው በደልና በኢሳትና በአጋሮቹ በሚካሄድበት
ዘመቻ ተጠቃሁ ብሎ
በስሜታዊነት ኣላስፈላጊ እርምጃዎች ከመውሰድ መቆጠቡ የሚያስመሰግን ነው። ከዚህ
ባሻገር ፅንፈኞቹ የሚያደርጉበትን
ጥቃት ተደራጅቶና ከሌሎች ወንድሞቹ ቅን ኢትዮጵያውያን ጋር ተባብሮ ሊመክተው
ይገባል። በተመሳሳይ መልኩ ልክ እንደ
ኦሮሞና ኣማራ ወንድሞቹ በተደራጀና ሰላማዊ በሆነ መልኩ ፍትሓዊ ስርዓት እንዲፈጠርመንግስት ላይ ተፅእኖ ሊያደርግይገባዋል።
በሌሎች ክልሎች
ያሉ
ኢትዮጵያውያንም
የጀመሩትን ሰላማዊ
ትግል መቀጠል
ይገባቸዋል።
ሆኖም ትግላቸው
ሰላማዊና
የትኛውንም
የህብረተሰብ ክፍል
የማያጠቃ ሊሆን
ይገባዋል። ለዚህም
የኦሮሞው ትግል
ውጤታማነት
ኣመላካች ነው።የኦሮሞው ትግል ማንንም ለይቶ ባለማጥቃቱና እጅን ወደላይ በመስቀል ሰላማዊ
እምቢታን በመጠቀሙ የመላውንኢትዮጵያዊ ድጋፍ ሊያገኝ ችሏል። በኣማራው ክልል በተካሄደው ተቃውሞ የታዩበትግሬው ላይ ያነጣጠሩ ፅንፈኛ
ኣመለካከቶች ለሺዎች ኣመታት በጋራ የኖረውን የኣማራና የትግራይ ህዝብ ታሪክየሚያጠለሹ ስለሆኑ የበለጠ ጉዳት
ሳያደርሱ ሊታረሙ ይገባቸዋል።
በአገር ውስጥ የሚገኙ ተቃዋሚ የፖለቲካ ሃይሎች እርስ በርሳቸው መነቋቆሩን ትተውህብረት መፍጠር ይኖርባቸዋል።
ህዝቡንም ለመምራት ዝግጁ ሊሆኑ ይገባል። በቁጣ የገነፈለውን የተቃውሞ ማእበል
መስመር ለማስያዝ የትግሉአላማዎችንና መደራደሪያ ነጥቦችን ማዘጋጀት ይኖርባቸዋል።
ተቃዋሚው ሃይል አንድ ወይም ሁለት ጠንካራ ቅንጅቶች
ወይም ደግሞ ግንባሮች ሊፈጥር ይገባዋል።
በውጭ የሚገኙ ተቃዋሚ የፖለቲካ ሃይሎች የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ጀምሮትእንደነበረው ኣገር ውስጥ ገብተው
በሰላማዊ ፖለቲካ ለመሳተፍ መዘጋጀት ይኖርባቸዋል። ኢትዮጵያን ማፈራረስ ዋና
ኣጀንዳው የሆነው ሻዕቢያ ስር የታቀፉ
ሃይሎች በፍጥነት ራሳቸውን ነፃ ማድረግ ይኖርባቸዋል።በውጭ አገር የሚገኙ የመገናኛ ብዙሃን ህዝብን ከህዝብ ከሚያጋጩ ተግባራት ተቆጥበው
ህዝብን የሚያስተባብርና አገሪቱን
ወደቀና መንገድ የሚወስዱ መልእከቶች ሊያስተላልፉ ይገባል። በተለይም ኢሳት በትግራይህዝብ ላይ የሚያደርገውን
ዘረኛ
ቅስቀሳ ባስቸኳይ
ሊያቆምና ኤዲቶሪያል
ፖሊሲውንም ሊመረምር
ይገባል። በኢትዮጵያ
ፖለቲካዊ ምህዳር ውስጥ
ምን
ኣይነት ሚና መጫወት
እንደሚገባው በጥልቀት
ሊመረምር ይገባል። ኢሳት
ገንቢ ሚናይጫወት ዘንድ ራሱን ከሻዕቢያ
ጥገኝነት ነፃ ሊያደርግ ይገባል። ከኢህኣዴግ ለውጥ እንዲኖር የምንጠብቀውን ያክል
ከተቃዋሚውም ለውጥ ያስፈልጋል።
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን እንዲለወጥ የምንታገለውን ያክል ኢሳትም
እንዲለወጥ መታገል ይገባናል።
ከሁሉም በላይ ለሰላማዊ ለውጥ ስኬታማነት ኢህኣዴግ መሪ ሚና ሊጫወት ይገባዋል።ኢህኣዴግ ጭንቅላቷን አሸዋ ውስጥ
እንደምትደብቀው ሰጎን ነባራዊ ሁኔታውን ከመካድ ይልቅ፣ ከሌሎች የፖለቲካ ሃይሎች ጋር
ለመደራደር ዝግጁ ሊሆንይገባል።
መጪው
የቀበሌና የወረዳ
ምርጫ ነፃ
እንዲሆን
ከማድረግ
ጀምሮ
አሸማቃቂውን
የኣሸባሪ ህግ
ማሻሻል፣ በዚያ
ህግመሰረት የታሰሩን ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች መፍታት ያስፈልጋል። ከዚያም በተጨማሪ
የምርጫ ቦርድ፣ የኢትዮጵያ
ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን እና ሌሎች
ተቋማት በነፃ ቦርዶች እንዲተዳደሩ
ማድረግ
ይገባል። እነኚህ መፍትሄዎችለኢህኣዴግ ለመዋጥ የሚጎመዝዙ ነገር ግን ኣገሪቱን፣ ህዝቧን እና ራሱን ኢህኣዴግን
ከጥፋት የሚያድኑ ብቸኛ መፍትሄዎች
ናቸው። ያለበለዚያ እጣችን እንደ ሶሪያና ሊቢያ እንዳይሆን የሚከለክለው ነገር የለም።
መርስዔ ኪዳንmersea.kidan@gmail.com1.
2.



3.
4.
5.
6.
7.
ከኢህአዴግ ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ
ትግሬዎች ላይ ያነጣጠረ ቅስቀሳ በኢሳት ቴሌቪዥን “ አሳን
ለማጥፋት ባህሩን ማድረቅ ”Resource Contribution Of NGOs In Primary EducationDevelopment In Tigray
EFFORT Group: Principal-Agent Problem: Mersea
Kidan
TPLF: From a change agent to a hindrance; Mersea
KidanThe 1994
population and
housing census of
Ethiopia
A ‘Nationalities in
Northern Ethiopia’
map; ‘Class
Struggle and the
Problem in Eritrea’
Ethiopian
Revolution
Information Center,
1979
አይጥ ለሞትዋ የድመት አፍንጫ ታሸታለች!
( ብስራት አማረ ማነው?)
ገብረመድኅን አርአያ
( ፐርዝ፣ አውስትራሊያ)
ተ.ሓ.ህ. ት ብሎ ራሱን የሰየመው የዛሬው ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ፋሺስቱ ፓርቲ፣ በየካቲት ወር 1967 ዓ.ም.ትግሉ ከጀመረበት
ቀን አንስቶ በትግራይ ሕዝብ የፈጸመውን አሰቃቂ የወንጀል ግፍ ብዙ ኢትዮጵያዊያን ያውቁታል።
የትግራይ ሕዝብ ያ የ 17 ዓመት የወያኔ ትግል “ ዘመነ እልቂት ” ይሉት ነበር። ዘመነ እልቂቱ ከደደቢት ትግራይ አልፎ
አሁን በኢትዮጵያ
ሀገራችን ሙሉ በሙሉ ሸፍኖ ወደ ‘ ዘመነ ጨለማ ” ተሸጋግሯል።
አሁን ለማንሳት የፈለግኩት፤ በውጭ አገር የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን ወገኖች ስለ ወያኔ ማንነትና ማወቅ ያለባችሁ
ጉዳዮች ብዙ ነገሮች
አሉ። እዛው በየአገሩ በምትኖሩባቸው ከተሞች ውስጥ የወያኔ ድርጅታዊ ተልዕኮ ለማሳካት ከትግራይ የመጡ
የፋሺስቱ ወያኔ ደቀ
መዛሙርት፤ በጥቅም የተገዙ አድርባዮች እና ካድሬዎች እንዲሁም ሰላዮች በመሆን በምትንቀሳቀሱባቸው
ማሕበራዊ እና ፖለቲካዊ
ወይንም ሃይማኖታዊ ሕይወታችሁ ውስጥ ተመሳስለው በመግባት አንድነታችሁን ለመበጥበጥ የተሰማሩ እንዳሉ
በተለያዩ ሰዎች
እንደተገለጸ ይታወሳል። ከተጠቀሱት የወያኔ ካድሬዎች ውስጥ በትግራይ ሕዝብ እና በኢትዮጵያ ላይ በማን
አለብኝነት ተነሳስተው ለብዙ
ኣመታት ሰብአዊ እና አገራዊ ወንጀሎችን የፈጸሙ እና ያስፈጸሙ የወያኔ እስር ቤት እና የስለላው መዋቅር
በሃላፊነት የሰራ ብስራት አማረ
ማን ነበር? የሚለውን ዛሬ ግልጽ ላደርግላችሁ እሻለሁ።
ብስራት አማረ ማን ነው?
ብስራት አማረ ትውልዱ አክሱም እስከ 9 ኛ ክፍል አክሱም አውራጃ የተማረ ሆኖ ወደ ህወሓት ትግል የተቀላቀለው
በ 1968 ዓ.ም. አጋማሽ
አካባቢ ነበር። ብስራት አሁንም የፋሺስቱ ወያኔ ምርጥ ታማኝ እና ሙሉ አባልነቱ እንዳለ ሆኖ በውጭ አገር እየኖረ
አሁንም የፋሺስቱ
የወያኔ ፖለቲካ እና ፖሊሲ አራማጅ እና ጠበቃ በመሆን በየራዲዮኑ እና ፓል ቶክ ስለ ወያኔ ብፁእነት ሲሰብክ
እያደመጥነው ነው። ያ
አልበቃ ብሎት አለቆቹን በመወከል ተቃዋሚዎችን በመዝለፍ አልፎም አገር ውስጥ በመሄድ በጌቶቹ ፍረድ ቤት
የክስ ማሕደር በመክፈት
ተቃዋሚዎችን ለማንገላታት እየሞከረ ነው። ይህ ደግሞ አዲስ ስልት እና አሳፋሪ ተግባር ስራየ ብሎ ተያይዞታል።
ህ.ወ.ሓ.ት. የተባለው
ድርጅት የፋሺስትነት ባሕሪይ እንዲኖሮውና እና በታጋዮችና በኗሪዎች ላይ ፋሺስታዊ ድርጊቶች እንዲፈጸም
አስተዋጽኦ ካደረጉት የወያኔ
ካድሬዎች አንዱ ብስራት አማረ እንደነበር ብዙ ታጋዮች ያውቁታል። ብስራት አማረ ዛሬ ውጭ አገር እየኖረ ወያኔንበመደገፍ ቢለፈልፍ
ሰው እየገረፈ እና እየገደለ ስለገነባው ድርጅት ጥብቅና ቢቆም ባሕሪያዊ ነውና መገረም የለብንም።
ብስራት አማረ ማን ነው?
ታሪኩን ትንሽ ወደ ኋላ በመመለስ እስኪ እንዳስስ። የተ.ሓ.ህ. ት (ህ.ወ.ሓ.ት) መሪዎች ከመነሻው ይዘውት የመጡ
የድርጅቱ የትግል መርሆ
ተግባራዊ ሲያደርጉት የነበረውን ፀረ ኢትዮጵያ፤ ፀረ አማራ፤ እና ፀረ ሕዝብ እንዲሁም በዋነኛነት ኤርትራን
ለማስገንጠልና አልፎም
የትግራይ ሪፑብሊክ መንግሥት ለማቋቋም አመራሩ ሲከተለው የነበረውን ፖሊሲውና አካሄዱ አብዛኛው ታጋይ
አገርና ሕዝብን የሚጎዳ
ጥፋት መሆኑን ከተገነዘበ በኋላ፤ አመራሩ እየተከተላቸው የነበረውን ጸረ ሕዝብ እና ፀረ ኢትዮጵያ እምነቶቹ ባጭሩ
መገታት አለበት ብሎ
በመወሰን ዲሞክራሲያዊ የሆኑ ጥያቄዎች በማስነሳት መንቀሳቀስ ጀመረ።
በታጋዩ ውስጥ የተንጸባረቀውና የተነሳው ቅሬታና እንቅስቃሴ በትግራይ ሕብረተሰብ ውስጥም በየቦታው ተመሳሳይ
ሆነ። ሕዝቡም የጥንት
ቅድመ አያቶቻችን እና ወላጆቻችን ደማቸውን እና አጥንታቸውን ከስክሰው የጠበቋትን እና ያስረከቡንን
ኢትዮጵያን ዛሬ የህወሓት
መሪዎች ከሻዕቢያ ጋር ተባብረው አገራችንን ሊበትኗት ነው የሚል ስጋት ከገጠር እስከ ትግራይ ከተሞች
ተንፀባረቀ።
በ 1968 ዓ.ም. መጨረሻ የወያኔ መሪዎች ይህ የታጋዩ እና የሕዝቡ እንቅስቃሴና ቅሬታ ስላስደነገጣቸው
በድርጅታችን ውስጥ ከመቀሌ፤
ከተምቤን፣ ከአዲግራት፣ ከራያና ከሁለት አውላዕሎ አውራጃዎች ተሰባስበው “ ሕንፍሽፍሽ ” (ብጥብጥ) ፈጠሩ
በማለት የተነሳውን
የዲሞክራሲ እንቅስቃሴ ለማዳፈን ተነሱ። ሃቁ ግን ታጋይ ሁሉ የተነሱት ቅሬታዎች በሰላማዊ እና በዲሞክራሲያዊ
መንገድ
ማንጸባረቃቸው እንጂ ህንፍሽፍሹን የፈጠሩት እራሳቸው አመራሮቹ ነበሩ።
በዚህ ጊዜ አመራሩ እንቅስቃሴውን ለመግታት ለኤርትራ የቆመበትን ፖሊሲውን ለማራመድ እና እንዲሁም
ፀረ- ሕዝብነቱ እና ፀረ-
ኢትዮጵያ እርምጃዎችን ለመውሰድ ያመቸው ዘንድ አመራሩ የሚከተሉትን እርምጃዎች በመውሰድ አፈና ማካሄድ
ጀመረ።
አመራሩ የወሰዳቸው እርምጃዎችበዚያው ወቅት የነበሩ የ ድርጀቱ ታዋቂ መሪዎች ስም ዝርዝር 1 ኛ ስብሓት ነጋ 2
ኛ መለስ ዜናዊ 3 ኛ አረጋዊ በርሄ 4 ኛ አባይ ጸሃየ 5 ኛ ስዩም
መሰፍን 6 ኛ ግደይ ዘርአጽዮን 7 ኛ አውኣሎም ወልዱ 8 ኛ ስየ አብርሃ 9 ኛ አጽብሃ ዳኘው ( በመለስ ዜናዊ የተገደለ)ተሰብስበው በ 1968
ዓ. ም መጀመሪያ ላይ 06 ( ሓለዋ ወያኔ/ እስር ቤት) እንዲስፋፋ በመወሰን በሁለት ደረጃ አስቀመጡት። ቀዋሚ እና
ተንቀሳቃሽ እስር ቤት።
1 ኛው - ቀዋሚ 06 ሓለዋ ወያነ የሚባለው፦በስፋት ሲከፈቱ 1- ቡምበት 2- ባኽላ 3- ዓይጋ 4- ወርዒ 5- ፃኢ 6- ዓዲ
በቅሎ 7- ዓዲ
ጨጓር 8 ሱር 9- በላሳ- ማይ ሓማቶ 10- ቆሎ ምሸላ..ወዘተ..ወዘተ.. ሲከፈቱ እነኚህን ለማንቀሳቀስ የተመረጡ
ሰዎች ለአመራሩ ታማኝ
የሆኑ ብቻ ነበሩ።
2 ኛው ተንቀሳቃሽ 06 ወይንም ሃለዋ ወያነ/Mobile የሚባለው ነው። ስራ ተግባሩ የሚከተሉትን የጭካኔ
እርምጃዎች፤ ዓለም አቀፋዊም
ሆነ ሃይማኖታዊ ወይንም ባሕላዊ ሕጎችን ሳይከተል በማን አህሎኝነት በጠመንጃ ጉልበት ተንተርሶ፤ መፈጸም ነው።
1.
ሰላመዊም ሆነ ተጋይ ወንድ፣ ሴት፣ ሽማግሌ፣ ቄስ፣ ድያቆን፣ ቃዲ፣ ሓጂ፣ ሸኽ ሳይል የፈለጋቸውን ጥፋት ይኑረው
አይኑረው
በስማ በለው እና በአሉባልታ ሰውን አፍኖ መጥለፍ (kidnapping)
2. በተለያዩ የትግራይ ከተሞች ውስጥ ድርጅቱ ነብሰ ገዳይ ተኳሾችን አሰርጎ በማስግባት የሚፈልጋቸውና
አብረዋቸው ድንገት
የቆሙትን ሲዝናኑ የነበሩትንም ያልተፈለጉ ንፁሃን ጭምር በጀምላ በተገኙበት ቦታ ሰልሎ በመግባት መግደል፡
3. በፈላ ውሃ እና በጋለ ብረት እስረኛን በአሰቃቂ ምርመራ ማቃጠል (Torture)
አመራሩ ከላይ የተጠቀሱት ክንዋኔዎች እንዲመራ ለብስራት አማረ ሃላፊነቱን ሰጠው። ወደ ዝርዝር ከመግባታችን
በፊት የሰውየው ገጸ
ባሕሪያት እኔ እንደማውቀው፣ ውሸት የሚያበዛ፤ ምቀኛ፤ አስመሳይ፤ አድርባይ፤ ለሰው ክብር የማይሰጥ ተሳዳቢ፤
ሰውን የሚንቅ፤ በትግሉ
ወቅት የሚያጎበድድላቸውን አለቆቹን በመመካት እና ከአለቆቹ የተሰጠውን ኃላፊነት ምርኩዝ አድርጎ በመመካት
ዝሙት በመፈጸም ሴትን
አስፈራርቶ የደፈረ ነው።
ከላይ የተጠቀሱት በሁለት ክፈሎች የተመደቡት የ 06 ዘርፍ ስራዎችን ሽብር ለማካሄድ በሃላፊነት የተመድቡ
ሌሎች ሰዎች አሉ። እነሱም፤-
1 ኛው ብስራት አማረ ዋናው መሪ 2 አሰፋ ጉሬዛ 3 ተስፋይ ጡሩራ 4 ታደሰ (06) 5 ትእግስት አሰፋ 6 ሉኡል በርሄ 7
ታደለ 8
ያለምብርሃን 9 ነፃነት ሰንደቅ ( ከትንሽ ጊዜያት በኋላ የተገደለ) እና አልፎ አልፎ አሰፋ ማሞ እና ሌሎች የመሳሰሉ
የዚህ የሽብር ቡድንአባሎች ይገኙበታል።
ዋና ተልእኳቸው
በሕንፍሽፍሽ የተበከሉ ታጋዮች (ሀ) ከሠራዊቱ ከየክፍሉ አፍኖ መጥለፍና ሓለዋ ወያኔ አስገብቶ በሰቆቃ ደብድቦ
ማስቃየት እና ከዚያ በኋላ
ስለ ሁኔታው በውሸትም በትክክልም እንዳፈለጋቸው ለመደባቸው አመራር ማቅረብ ነው። አመራሮቻቸውም
ለስልጣናቸው ማጎልበቻ
እስከ ጠቀመ ድረስ በሰው ሕይወት የሚደርሰው ጉዳት ጉዳያቸው አልነበረምና ስለ ሆነም ማጋጣዎቹ
ካድሬዎቻቸው እንደ የናዚዎቹ
የጎስታፖ ቡድኖች የፈለጉትን ሽብር በማንኛውም ሰዓት ወቅት ቀን ይሁን በውድቅት ሌሊት የማፈን የመግደልና
የማስፈራራት ተግባር
በፈለጉት ሰው ላይ የመፈጸም ሙሉ መብት ነበራቸው። ጥፋት አደረጋችሁ ተብለውም የሚጠይቃቸው ዓለም
አቀፋዊም ይሁን
ሃይማኖታዊ ወይንም ባህላዊ አካል በስልጣናቸው ዙርያ የለም። ሁሉም በጁ ሁሉም በደጁ በጫካም ይሁን ዛሬም
ስልጣናቸው የማይገሰስ
ባለሙሉ ስልጣን ነገሥታቶች ናቸውና የተጎዳው ሰው ቤቱ
የኢ.ድ. ሕ አባል፤
የደረግ እና የኢሕአፓ አባል እና ሰላይ፣ ፀረ ኤርትራ ነፃነት ነህ ወይንም ነሽ እየተባሉ ከላይ በተጠቀሱት የሽብር
ቡድን አንቃሳቃሾች ትእዛዝ
እና ተሳታፊነት ከየከተማውና ገጠሩ እየታፈኑ ለነ ብስራት አማረ እየተላለፉ በመስጠት ብዙ ሰብአዊ ጉዳቶች
ተፈጽመዋል። እነኚህ የሽብር
ቡድኖችና መዋቅሮች ተልእኳቸው ሽብር በማካሄድ ዲሞክራሲያዊ መብቶችን አፍኖ ሕዝቡ ለድርጅቱ ሙሉ ተገዥ
ሆኖ በፍርሃት
እንዲንበረከክ ማድረግ ነው።
እንግዲህ የሽብሩ መልክ እና ስፋት ሰፊና የተለያየ መልክ ቢኖሮውም አመራሩ በድርጅቱ ውስጥ ሕንፍሽፍሽ
ተፈጥሯል ብሎ ራሱ አመራሩ
የፈጠረው ሽብር በታጋዩ ውስጥ በጣም በርካታ ታጋዮች ከ 1969- 1975 መጨረሻ የቀጠፈው ያጠፋው ህይወት
ዘርዝሮ ለመጻፍ በዚች
አጭር ፅሑፍ አስቸጋሪ ነው። ቢሆንም ብስራት አማረ ከነ ቡዱኑ አመራሩ በሰጠው ሃላፊነት የፈፀመው ግፍ ግድያ
የሰቆቃ ድብደባ ባጭሩ
ከነመረጃው አቀርባለሁ።
ብስራት አማረ ከ 1969 ዓ.ም. ጀምሮ በሕንፍሽፍሽ ተለክፈዋል እየተባሉ ያጠፋቸው ጥቂቶች ከማውቃቸው ሰዎች
መካከል፤1.
2.
3.
4.
አበራ ማንካ ( በብስራት አማረ የተገደለ ነገር ግን እራሱ ገደለ ተብሎ በአመራሩ ለሽፋን የተነገረለት)
ተስፋይ ( ተስፋይ ህንፍሽፍሽ ተብሎ በአመራሩ የቅጽል ስም የተሰጠው) ብስራት አማረ በሰቆቃ ( በቶርቸር
አሰቃይቶ) የገደለው፡
ወዲ ሓኔታ እንደ ተስፋይ በሰቆቃ የተገደለ
ኪዳነማርያም በላይ - የፈላ ውሃ ጭንቅላቱ ላይ ተደፍቶበት የሞተ፤5.
6.
7.
8.
9.
10.
11.
12.
13.
14.
15.
16.
17.
ኃ/ ሥላሴ ገ/ ሚካኤል በድብደባ እና በጋለ ብረት የተገደለ፤
አባዲ ተምቤን (ጎልያድ) በብስራት አማረ የተገደ ( ወያኔ የሚለው ራሱ የገደለ)
ጐይቶኦም አብረሃ
ዳዊት ግምባር (ሕንፍሽፍሽ)
ግርማይ ዘርኦም
ብስራት አለማየሁ
ሐጐስ ኃይለስላሴ
ሐድሽ ዮሐንስ
ንግሥቲ
ግደይ
ዘርኡ በዛብህ
ሙሉጌታ አብርሃ
አዛናው ገ/ ጻድቕ ( ይህ ታጋይ ከመለስ ዜናዊ እና ከስብሐት ነጋ ጋር በነበረው ቅራኔ ብስራት አማረ ዛና ወረዳ አካባቢ
አፍኖ
አጠፋው
18. ባሻይ ሐንጣል19. ተኽላይ
20. ክንፈ ራያ ወዘተ ናቸው።
እነዚህ ለምሳሌ የተጠቀሱት ባሕርን በማንኪያ እንደመጨለፍ የቀረበ እንጂ ረጋ ብሎ በጥናት ይቅረብ ከተባለ በጣም
በርካታ ሕይወት
ብስራት አማረ በሚመራው የሰቆቃ እና የስለላ ዘርፍ የተገደሉ እና ከየክፈላቸው እየተለቀሙ ታፍነው ደብዛቸው
የጠፉ እጅግ በጣም፤
በጣም ብዙ ናቸው።በሰቆቃ ማለት በፈላ ውሃ በድብደባ በጋለ ብረት በእሳት እየተሰቃዩ የጠፉ በርካታ የሰዎች
ህይወት ተጠያቂዎቹ
አመራሮቹ እነ ስብሓት ነጋ እና እነመለስ ዜናዊ እንዲሁም በሰው ልጆች ላይ ክፉ ሰቆቃ ሲፈጽሙ ከነበሩት መካከል
ሰው እያፈነ የሕዝብን
ሰላም በፍርሃት ሲያስሸብረው የነበረው “ የወያኔ ጀስታፖው ” ቡድን መሪ ብስራት አማረ እና መሰሎቹ ለተፈጸሙት
ኢሰብአዊ እርምጃዎች
በሃላፊነት ተጠያቂዎች ናቸው።
የብስራት አማረ የሽብር ቡድን እና ተግባር እስከ 1975 ዓ. ም በተቀናጀ የአፈና እና የግድያ እንቅስቃሴ ያለምንም
ተጠያቂነት አሁንም ወደ
ሰላመዊ ነዋሪ ሕዝብ ተሸጋገረ።ለምሳሌ ከሕዝቡ መሃል እየታፈኑ የውሃ ሽታ ሆነው እዚህ ቀሩ ሳይባሉ እየታፈኑ
የተገደሉት ጥቂቶቹን
ልጥቀስ።
በ 1971 ዓ.ም. መጀመሪያ አካባቢ ብስራት አማረና በስራ ከሚገናኘው በመቀሌ አካባቢ የከተማ የሕዝብ ግንኙነት
ኃላፊ የነበረው
አለማዮህ በቀለ ከሚባለው ሃገረ ሰላም ኗሪ የሆኑ በጠላ ንግድ የሚተዳደሩ ሁለት ወጣት ሴቶች በተደጋጋሚ
አስገድደው ከደፈሯቸው
በኋላ ድርጊታቸው በታጋዩ እና በሕዝቡ እንዳይጋለጥባቸው የደርግ ሰላዮች ናቸው በማለት በብስራት አማረ ሪፖርት
ተዘጋጅቶ በሌሊት
ከመኖሪያ ቤታቸው አፍኖ በመውሰድ ያጠናቀረውን ሪፖርት ለስብሓት ነጋ አቅርቦ በሁለተኛው ቀን በሓለዋ ወያነ
አባሎች በጥይት
ተደብድበው እንዲረሸኑ ተደርጓል።
በ 1972 ዓ.ም. ብስራት አማረ እና አፋኙ ጉጅሌው ከማይጨው ወደ መቀሌ በሚወስደው ዋና መንግድ ላይ አድፍጦ
በመጠበቅ አንዲት
መኪና ሰዎች ጭና ወደ መቀሌ አቅጣጫ ስትጓዝ ቤት ማራ በሚባለው ቦታ አስቁሞ 6 አስተማሪዎች 2 ከደሴ
የመጡ የመንግሥት
ሠራተኞች ከመኪናው እንዲወርዱ በማድረግ አስገድዶ በመጥለፍ ፃኢ ወደ ሚባል አካባቢ ወሰዳቸው። ብስራትአማረ እነኚህ ሰዎች
ከጠለፈ በኋላ ብዙ የመቀሌ ኗሪ የሚያውቀው በቅጽል ስም “ ጥንቸል ” እየተባለ የሚጠራው እና አራት
አስተማሪዎች እንዲሁም ሁለት
የደሴ ሰዎች በጠቅላላ 6 ቱ ሲገደሉ የዓድዋ ተወላጆች የሆኑት የተቀሩት ሁለት አስተማሪዎች ግን በነፃ ለቀቃቸው።
ሲገደሉም ብስራት
አማረ ለአባይ ፀሃየ ስለተጠለፉት ሰዎች ጉዳይ እንዲገደሉ ብሎ ሪፖርት አቅርቦለት ይገደሉ አለ፡ብስራትም
እንዲገደሉ አደረገ።
ሌላው አሳዛኝ ድርጊት በ፶አለቃ በላይ የሚባል ተመርተው በሰላም እጃቸው የሰጡ የኢትዮጵያ የደርግ ወታደሮች
በብስራት አማረ የተዘጋጀ
ሪፖርት ለመስ ዜናዊ እና ስብሐት ነጋ ከተሰጠ በኋላ በሙሉ አማራዎች ስለነበሩ ግደሏቸው ተብሎ 1 ብስራት
አማረ 2 ክንፈ 3. ገ/መድኅን
4. አለምሰገድ እይንቺ 5. ሐሰን ሽፋ ሆነው ከ 06/ ባዶ ሽድሽተ/ ከሓለዋ ወያነ አባላት ጋር በመተጋገዝ በሚጠጡት
ውሃ ላይ መርዝ
ተጨምሮበት ውሃው እንዲጠጡት ተደርጎ አብዛኞዎቹ ወዲያው ሲሞቱ በሞት አፋፍ ሲግሩ የነበሩት ቀሪዎቹ
ደግሞ በጋለ ብረት ሆድ
እቃቸው እያስገቡ ጨረሿቸው። ጊዜው በ 1972 ዓ.ም. ወርዒ ውስጥ ነው።
በሰላማዊ ትግራይ ዜጎች ላይ ተፈጸመ አፈና እና ግድያ አሁንም ብስራት አማረ ከአሸባሪው የወያኔው ጀስታፖ
ቡድን በመንቀሳቀስ በቀንም
በሌሊትም እያፈነ የወሰዳቸው ኗሪዎች፤
1. ፊታውራሪ ብፁእ ወ/ ጊዮርጊስ እንደርታ
2. ቀኛ/ ኪሮስ ዓድዋ 3. ቀኛ/ ኃይለስላሴ ዓድዋ
4. ግራ/ ታደለ ማሩ ተምቤን
5. አቶ ወርቀ ልዑል ተምቤን
6. ፊታውራሪ ዘገየ ክለተ አውላዕሎ
7. ግራ/ በላይ ገብሩ ተምቤን
8. አቶ ኪዳነ ሐጐስ
9. ወ/ ሮ አባዲት
10. አሰፋው ወልደ አረጋይ ዓድዋ ይሓ
11. ቄስ አርአያ ዛና
12. ቀኛ/ እምብዛ ዛና
ወዘተ... የመሳሰሉ ሰዎች በብስራት አማረ መሪነት እየታፈኑ መድረሻቸው የጠፋ የውሃ ሽታ ሆነው ቀርተዋል።
በእነ ብስራት የሚመራው አሸባሪው ቡድን በፈለገው ቦታ እየተንቃሰቀሰ ሕዝብን ሲያፍን በሽሬ አካባቢ ደግሞሌላው በህወሓት አሸባሪው
የስለላ እና የምርመራ እንዲሁም የእስር ቤት ሰቆቃ ፈጻሚ ቡድን ሽሬ ውስጥ በእነ አበበ ተክለኃይማኖት
(ጆቢ/ዑስማን) እነ አውዓሎም
ወልዱ፤ ታደለ እና የመሳሰሉ በብዙ ሰዎች ላይ ሰቆቃ ሲፈጽሙ ነበር። ለምሳሌ-
1 ሃለቃ ገ/ ሚካኤል 2. አቶ ገብረሊባኖስ መዝገቦ 3. አቶ ገዛኢ ረዳ 4. አቶ ተወልደ ገ/ ሥላሴ 5 አበበ ገ/ ማርያም 6.
አቶ ሙሉጌታ ደስታ
7. አቶ በላይ ባህታ 7 ቄስ ጽጌ 8. አቶ ወልደ ንጉሥ 9. አቶ ገብረጻድቅ ጸጋይ 10 ሃለቃ ጥላሁን እና በ እድሜ እጅግ
ወጣቶች የሆኑትን
ሳይቀር በሰቆቃ እየተሰቃዩ በጥይት ተደብድበው ተገድለዋል። ከላይ የተጠቀሱት ሰዎች የሸሬ አውራጃ ተወላጆች
ናቸው።
ብስራት አማረም በበኩሉ ሌላው የሽብር ቡድን በመምራት ከ 1970-1972 ዓ.ም. በየከተማው የፈጸሙትን ሽብርና
ግድያ እንደገና
እንመለክት።
ዓድዋ፦ በ 1971 ዓ.ም. አካባቢ ዓድዋ ከተማ ከቀኑ 11 ወ/ ሮ ጉንቦወርቅ የሚባሉ ጠጅ ነጋዴ ቤት በመግባት እጅ
ወደላይ ብሎ
ያስገደላቸው ሰዎች 1. መምህር ይሕደጐ 2. አቶ ብርሃነ ኪ/ ማርያም 3. ፍስሃ የሚባል ወጣት ነጋዴ 4. አቶ ቢተው
ብርሃነ ጠጅ ቤቱ
ውስጥ እያሉ ሲገደሉ ከመጠጥ ቤቱ ውጭ ደጃፍ ላይ የተገደሉ ደግሞ 1. አቶ አብርሃ አበራ 2. አቶ ገብረዝጊ
ዓለማየሁ ይባላሉ። የመጠጥ
ቤቱ ባለቤት ወ/ ሮ ጉንቦወረቅ ታፋቸው ተመቱ፣ ግን አልሞቱም ። አቶ ተፈሪ ተክለሃይማኖትም እግራቸው
ተመትተው ቆሰሉ። በዚህ
መልክ የብስራት አማረ የሽብር ኦፐረሽን ቡድን 6 ሰዎች ገድሎ 2 ሰዎች አቁስሎ ወጣ።
አክሱም፦ በመግድያ ፈጻሚ ክፍል (ፈዳይን) የተሰማሩ አክሱም ተወልደው አክሱም ያደጉ የከተማው መውጫ እና
መግቢያ የሚያውቁት
የአክሱም ልጆች እና ብስራት አማረ ከሚያስተባብረው የሽብር ግድያ የአፈና የእስራት እና የስለላ ቡድን ጉጅሌውን
መርቶ አክሱም ከተማ
በመግባት መምህር መልአኩ መንገሻ እና ሁለት አስተማሪዎች አስገድሎ አንድ ተማሪ አቁስሎ ወጣ።
መቀሌ፦ ብስራት አማረ ከነቡዱኑ መቀሌ ከተማ ተሽሎክሉኮ በመገባት አለነ ቢሆን የሚባለው ታጋይ ከበረሃ
ሸሽተው እጃቸውን ለደርግ
የሰጡ እና የግ.ሓ. ት ( ግምባር ሓርነት ትግራይ) አባሎች የነበሩ ከወያኔ እስር ቤት ከሞት አፋፍ ያመለጡትን እነ
ተፈራ እነ ሃይለኪሮስ
የመሳሰሉት ለመግደል መድኅን መልጐም ወደ ተባለ ቡና ቤት አለነ ቢሆን የተባለ የበረሃ ታጋይ ገብቶ ሁሉም መጠጥእየጠጡ እዛው
ባሉበት እንዲረሽናቸው በመግባት ሁለት ሰዎች ገድሎ ከቡና ቤቱ ለማምለጥ ሲሞክር ከቡና ቤቱ ውስጥ ከነበሩት
ሰዎች በተተኮሰበት
ጥይት ህይወቱ አልፎ የነብሰ ገዳዮቹ ቡደኑ እና የስለላው አቀነባባሪ እና መሪው ብስራት አማረ ግድያውን አስፈጽሞ
ወደ በረሃው ተመለሰ።
ሽሬ - ብስራትና ጉጅሌው ሽሬ ከተማ ገብተው ተከስተ አሰፋ የሚባል የፊታ/ አሰፋ ልጅ ከሦስት ጓደኞቹ ጠላ ቤት
ገብተው እየጠጡ
ሲዝናኑ ብስራት እና ጉጅሌው ተከታትሎ በመግባት ተከስተ አሰፋ እና ሦስቱ ጓደኞቹ ገድሎ አንድ አዛውንት
የፖሊስ ጡሮተኛ አቁስሎ
ወጣ። ብስራት አማረ በሁለት አውላዕሎ እና አዲግራት እና በተለያዩ የትግራይ ከተሞች ሰላዮች እና ነብሰ ገዳዮች
(ፈዳይን) በማሰማራት
ተመሳሳይ ሽብር በሰው ህይወት ላይ መውሰዱ ይታወቃል። ብስራት አማረ በነበረው የደህንነት፤ የስለላ እና የእስር
ቤቶች ( ሓለዋ ወያነ)
ሃላፊነት ሲፈጽመው የነበረው የህ.ወ.ሓ.ት. ሽብር ስራ አሁንም እስከ 1978 በጥልቀት ሲያስፈጽም የነበረው
የአፈና፤ የመግደል ሰቆቃ
ተግባር በተደራጀ መልኩ ቅርንጫፎቹ እንደተስፋፉ መዋቅሩ እንደሚከተለው ተዘርግቶ ነበር፡
ፖሊት ቢሮ የበላይ ሃላፊዎች
መለስ ዜናዊ፥ ስብሓት ነጋ፥ አባይ ጸሃየ
የደኅንነት ዋና ሃላፊ
ክንፈ ገ/መድኅን
የሓለዋ ወያነ የበላይ ተጠሪዎችሓሰን ሽፋ፣ ቢተው በላይ፣ ብስራት አማረ፣ ዘርአይ ይሕደጎ ( ዘርአይ ማንጁስ)
የስለላ እንዲሁም የሲቪል እና ሙርኰኞች እስር ቤት
የሴት ሲቪል እስር ቤት(063)
የወንድ ሲቪል እስር ቤት (062)
የሙርኰኞች እስር ቤት (061)
ወዲ ሻምበል፣ አበበ ዘሚካኤል፣ ታደሰ መሰረት
የታጋዮች እስር ቤት
የሴት ታጋይ እስር ቤት (065)
ወንድ ታጋይ እስር ቤት (064)
እነኚህ አምስት ዋና ዋና ክፍሎች ሰቆቃ የርሸና/ ግድያ የአፈና ስራዎች የሚካሄድባቸው ፈጻሚ እና አስፈጻሚ
ክፍሎች ናቸው።
ከዘሚካኤል ለገሰ ( ወዲ ሻምበል) ስር064 የሚቆጣጠረው ታደሰ 065 ደግሞ ብርሃነ ሲሆኑ
ከብስራት አማረ ስር
061 ካሕሳይ ቆራጽ
062 ግደይ ወዲ ፊውዳል
063 ወዲ ኮበል የመሳሰሉት አሉበት።
እነኚህ እስር ቤቶች የሚገኙት “ ግህነም ” ከሚበላው ቦታ ፀገዴ ውስጥ ነው። እስረኞች የሚታሰሩበት ክፍሎች
ብዛት እስከ 150 ክፍሎች
ሚደርሱ ሲሆኑ፤ ከመሬት በታች ሁለት ሜትር ጥልቀት ተቆፍሮ ከመሬቱ ተመሳስሎ የተሰራ በ 4,500 የወታደር
ሙርከኛ እስረኞች
ጉልበት ነበር የተገነባው። ተገደው ይህ እስር ቤት የሰሩት ሙርኰኞችም እዛው ገብተው እንዲታሰሩ ተደረገ።
ይህ ቦታም አሰቃቂ እና ሰቆቃ የሚካሄድበት አስፈሪ እስር ቤት የሚጠብቁት ዘበኞች ብዛት 500 ታጋዮች ሲሆኑ
ሁሉም ጉልበተኞች እና
ደንዳና ቁመና ያላቸው ምልምል ታጋዮች ናቸው። መጀመሪያ የተረሸኑት እንኚህ 4,500 የሚሆኑ እስር ቤቱን
የቆፈሩት ሲሆኑ ከመላው
ኢትዮጵያ ጎሳዎች የተውጣጡ ወታደራዊ ምርኰኞች ይሁኑ እንጂ አብዛኛዎቹ አማርኛ ተናጋሪ አማራዎች ነበሩ።
ምርኮኛ እየተባላ በሰላም እጁን የሰጠ ደርግ ካድሬዎች፤ የደርግ አባል፤ የደርግ አገልጋይ ወ.ዘ.ተ. እየተባለ ሴቶችም
ሳይቀሩ ከጐንደር፤
ወሎ፣ ጐጃም በገፍ ወደ እዚሁ የምድር ገሃነም እየተወሰዱ በብዙ ሺሕ ሚቆጠሩ ሕይወት በመለስ ዜናዊ፣ በሰብሓት
ነጋ እና አባይ ፀሓየ
አርከበ ዑቕባይ የመሳሰሉት የዛው ግደለው ደብድበው አፍነው የሚል ትእዛዝ በመስጠት ትእዛዛቸውን
ለሚፈጽመውና ለሚአስፈጽመው
ለብስራት አማረ በሚተላለፍለት መመሪያ ተረሻኞቹ የሚቀበሩበትን ጉድጓድ ተቆፍሮ በጅምላ የተቀበሩ ሰዎች
መቃብር በዓይኑ ያየ ሰው
ዘግናኝ እና አስፈሪ በመሆኑ ጤነኛ እንቅልፍ መተኛት ያስቸግራል። በጣም የሚገርመው 10 ሺህ ሰው ገድያለሁ ሲል
የተደመጠው ብስራት
በሰው ልጆች ላይ የፈጸመውን ግፍ ይቅርታ ጠይቆ ከመጸጸት ይልቅ አሁንም አሜሪካ አገር እየኖረ ለአለቆቹ ጥብቅና
ቆሞ ማየት እጅግ
ያሳዝናል።
ውድ ኢትዮጵያውያን ሆይ!
በብስራት አማረ እጅ በጥይት ተደብድቦ የተረሸነው ዜጋ እሱ ከሚያምነው በላይ እጅግ በርካታ ህይወት ጠፍቷል።
ብስራት አማረ በነበረው
የስለላ፤ የምርመራና የእስር ቤቶች ተቋም እና የፈዳያን/ የገዳይ ቡድን አቀናባሪነት ስልጣን ተጠቅሞ በፈጸመው ግፍበሕግ ቋንቋ ጀነሳይድ
ነው። ለፈጸመው ወንጀል በዓለም የሰብአዊ መብት ተማጓች ፍረድ ቤት መቅረብ አለበት። ይሄ ካልሆነ የሰው
ህይወት ከድመት ህይወት
ጋር የሚያወዳድሩት እነ ብስራት አማረ የመሳሰሉ የህ.ወ.ሓ. ት ቁልፍ ሰዎች በሰው ልጆች ደም እያላገጡ
መኖራቸውን ሊቀጥሉ ነው ማለት
ነው። ይህ ሁሉ ደም አፍስሰው ለሰው ልጆች መብት እና ዲሞክራሲ ተቆርቋሪ ንጹሃን ነን ሲሉ ላደመጠ
ውስጣቸው ለሚያውቅ ሰው እጅግ
ይዘገንናል። ስለዚህ ባንድነት ሆነን አቤት ማለት አለብን። ይባስ ብሎ አፋቸው መዝጋት ሲገባቸው እና የሰሩት ግፍ
ሳይቆጫቸውና
ይቅርታ ከመጠየቅ ፈንታ የበደሉትን ዜጋ እንደገና ሳያፍሩ ሲዘልፉት እና ከተሰደደበት አገር ሰላም ሲነሱት ይታያሉ።
ፋሽስቱ፤ ነብሰገዳይ፤ ሽብርተኛ እና ቅጠረኛው ህ.ወ.ሓ. ት በግንቦት ወር 1983 ዓ.ም. ኢትዮጵያ እንደተቆጣጠረ
1- ብስራት አማረ 2-
ታደሰ መሰረት 3- ዘርአይ ይሕደጐ/ ዘርኣይ ማንጁስ በቀጥታ ማእከላዊ ምርመራ በሰቆቃው ማእከል ውስጥ
ተመደቡ። ከ 1983 ዓ.ም
ጀምሮ ‘ መላ አማራ ሕዝብ ድርጅት ’ በሚባለው ሰላማዊ ድርጅት በአባሎች እና አመራሮች ላይ ብዙ የሰቆቃ
መርመራ በማካሄድ ባልዋሉት
ወንጀል ፈጽመሃል እየተባሉ አዲስ አበባ ማእከላዊ ምርመራ ድረስ ከየክፍለሃገሩ እየተለቀሙ ሰቆቃ
እንዲፈጸምባቸው ቁልፍ የደህንነትሰልጣን በመያዝ ተዋናዮች ከነበሩት በርካታ የህ.ወ.ሓ.ት. ባለስልጣኖች አንዱ
ብስራት እና ከላይ የተጠቀሱ እና የመሳሰሉ አረመኔዎች
ናቸው። እነ ፕሮፌሰር አስራት ስቃይ የዚህ ነብሰገዳይ እና ሕብረተሰብ አሸባሪ ቡድን ውጤት ነው። እነ አሰፋ ማሩ
የተገደሉት በዘርአይ
ይሕደጐ እና ግበረ አበሮቹ ነብሰገዳዮች ነበር። አንደነት ቢኖረን እና በዚህ ዓለም ሕግ የሚከበር ቢሆን ኖሮ እነ
ብስራት አማረ በሰው ልጆች
ህይወት ቀልደው ሲያበቁ ዛሬም እየተንደላቀቁ ስለ ዲሞክራሲ እና የሰው ልጆች መብት መከበር በወያኔ ጀሌዎች
የሚካሄዱ የዜና ማሰራጫ
ማእከሎች እየተጋበዙ ሕሊናቸውን ሳይወቅሱ እንደ ፒላጦስ ከደሙ ንጹህ ነን እያሉ ባልዘላበዱ ነበር። ጠመንጃ
አንግበው በዜጎች ላይ
የሰሩት ግፍ [በሞት] የሚያስቀጣ ወንጀል ነው የፈጸሙት። እነዚህ ሰዎች አንድ ቀን እንኳ ስህተት ፈጽመናል
አላሉም።
እነ ብስራት አማረ “ ሽብርተኛው እና ነብሰ ገዳዩ ወያኔ ” ኤርትራ እንዳስገነጠለ የኢትዮጵያ ጥቅም እና ሉአላዊነት
አልተከበረም ብለው
ያዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሰላማዊ ሰልፍ ሲያደርጉ፤ እንደ ዱር አራዊት በፖሊሶች እየታደኑ እና እየተዋከቡማእከላዊ እና
የመሳሰሉት አሰቃቂ እስር ቤቶች እየተወረወሩ የተገረፉ እና ልዩ ልዩ ሰቆቃ የተፈጸመባቸው ስናስታውስ የእነ ዘርአይ
ይሕደጐ እና ብስራት
አማረ የገነቡት የስለላ እና የሽብር ቡድን ያከናወነው ዘግናኝ ግፍ ብዙ ተማሪ የሚያስታውሰው ወቅት ነው።
በ 1984 ዓ.ም. በአርባ ጉጉ እና በሌሎች ቦታዎች ብስራት አማረና አጋሮቹ የሲቪል ልብስ ለብሰው በወቅቱ የነበረው
ጠቅላይ ሚኒስቴር
ታምራት ላይኔ፤ መለስ ዜናዊ፤ በረከት ስምኦን እና የመሳሰሉ ባለስልጣኖች ትእዛዝ እና እውቅና ያለ ቦታው የሚኖር
ተስፋፊ ነፍጠኛ እያሉ
ከተገንጠይ ቡድኖች ጋር አባሪ አስተባባሪ ሆነው በአማራው ሕብረተሰብ ላይ ለተፈፀመው ግፍ ተጠያቂዎች ናቸው።
በመጨረሻ ላይ
በጠመንጃ ሃይል ተማምነው በዜጎች ላይ ቁጥር ስፍር የሌለው ግፍ ከፈጸሙ በኋላ ባዲስ አበባ ኗሪ እና በሌሎቹ
ዓይን ውስጥ ስለገቡ
ስብሓት ነጋ እና መሰል አለቆቻቸው ድጋፍ ታክሎበት ዘርአይ ይሕደጐ/ ዘርአይ ማንጁስ ወደ እንግሊዝ አገር
ለትምህርት ብለው ላኩት።
ብስራት አማረ ደግሞ ወደ አሜሪላ ላኩት። የሁለቱ ድብቅ ተልእኮ ግን ዘርኣይ ማንጁስ አውሮጳ ውስጥ ካሉት
የትግራይ ተወላጆች
አስተባብሮ ስደተኛው እና ተቃዋሚ ሃይሎችን እንዲሰልል ( በነገራችን ላይ ዘርኣይ በማዕርጉ የወያኔ ሻምበል ነው)
በዚህ እንቅስቃሴ
ተሰማርቶ የዓድዋ የሽሬ የአክሱም ተወላጅ ተባባሪዎች ሲያገኝ የስለላ ትምህርቱን እየተማረ በተሰማራው
ተልእኮም እየፈጸመ ይገኛል።
በዚህም ወያኔ ከፍተኛ የገንዘብ ጠቀሜታ እና እንክብካቤ ይደረግለታል። ዘርአይ ማንጁስ ትውልዱ አክሱም ነው።
ብስራት አማረም ያው ትውልዱ አብረው አክሱም ናቸው። ብስራት ‘ ጅብ በማያውቁት አገር ሄዶ ቁርበት
አንጥፉልኝ አለ ’ እንደሚባለው
የፈጸመው ግፍ እና ሰብአዊ ወንጀል አይታወቅብኝም በሚል ራሱን በማታተለል ጨዋታ ተጠምዶ አሜሪካ ውስጥ
ሆኖ ኢትዮጵያውን
የወያኔ ተቃዋሚዎችን ሲዘልፍና ለሻዕቢያ ጥብቅና ቆሞ የሻዕቢያን ፖሊሲ የሚቃወሙ የትግራይ ህወሓት ታጋዮችና
ኗሪዎችን ሲያሸብሩ
ከነበሩት ከነ ኰሎኔል ይትባረክ የመሳሰሉ ከጥቂት እሱን መሳይ የወያኔ ካድሬዎች ጋር ሆኖ ሕብረተሱን በመከፋፈል
በየቤተክርስትያኑ እና
ትግራይ ተወላጆች ማሕበራት እጁን እያስገባ አንድነት እንዳይኖር የመለስ እና የስብሓት ነጋ ተልእኮ ለብዙ ዓመታት
ያለ ስጋት በመፈጸም
ላይ ይገኛል። ያ አልበቃ ብሎ አሉላ አባ ነጋ በተባለ የመለስ ዜናዊ ካድሬዎች ፕሮፓጋንዳ መጨፈሪያ ፓል ቶክውስጥ እሱ እና ኮሎኔል
ይትባረክ በመሆን እኔ ባቀረብኩት የ 1977 ቱ የዝርፍያ ሰነድ ከመተቸት ይልቅ አንዴ “ ሊሆን ይችላል ” ሲል አንዴ
ደግሞ “ ገብረመድኅን
አርአያ ተደረገ የተባለው ዝርፍያ የሚያውቅበት ስልጣን ወይንም ግንኙነት አልነበረውም ” እያለ የአለቆቹን
ንቅዘት/ ሙስና እና አምባገነንነት
ለመከላከል ከመዘላበድ አልፎ እኔኑን ወደ ተራ ዝልፊያ በመግባት ከንቱ ሙከራ ማድረጉ ስታዘበው፤ ይሉኝታ
የማያውቅ አንድ ፍጡር
ባደባባይ እርቃኑን ጥሎ ቢራመድም ደንታ እንደሌለው ያሳያል። ለድርቅ የተሰጠ ዕርዳታ ሁኔታ ማወቅ ከነበረበት
እንደ እነ ተኽለወይኒ
አሰፋ የመሳሰሉት እንጂ ገ/ መድኅን አርአያ የሚያውቀው ነገር የለም ሲል ፓል ቶክ ውስጥ ተናግሯል ሲሉ ሰዎች
ነግረውኛል። ስልጣን
ካልነበረኝ ተክለወይን አሳፋ እና እኔ አርዳታ ከሰጡት ፈረንጆች ጋር ቁጭ ብየ ገንዘብ እየቆጠርኩ የሚያሳየው ዓለም
የተመለከተውን
የቢቢሲውን ፎቶግራፍ “ ገ/ መድኅን አርአያ ከሁኔታው ጋር የተያያዘ ስልጣን ካልነበረኝ የብስራት አማረን ምሳ እና
እራት ቂጣ ስጋግር
የተነሳሁት ፎቶ ነው ሊል ነው?” የመለስ ዜናዊ ካድሬዎች እና ብስራት አማረ ለማያውቃቸው ሰው ውሸታቸውን
ሲዘላብዱ ለሚሰማ
እውነት ይመስላቸው ይሆናል። ለዚህም ነው ሰውየው ውሸታም ነው የምላችሁ። አውነታው ለምናውቀው ግን
ከሚዘላብዱት ቅጥፈት
የተለየ ጉድ የተሸከሙ ጉደኞች ናቸው። የትግራይ ተወላጆች ከነዚህ ውሸታሞች ራሱን ማግለል አለበት። ያ ሁሉ
ግድያና ግፍ ፈጽመው
ምንም የማይሰማቸው አረመኔዎች ናቸው። ሳይነካ ኑ ንኩኝ እያለ የሚወተውት ለችግር ራሱን የሚጋብዝ ፍጡር
እንደ ብስራት አላየሁም።
ብስራት ለወያኔ መቆሙ የራሱ ፍላጎት ነው። ነግር ግን ከሰራው ገበና ሳይጸጸት እንደ ገና በላያችን ላይ ሊወጣብን
ሲሞክር አስገራሚ ነው።
ወያኔ በግፍ የተጨማለቀ ድርጅት ነው። አንድ ቀን በግህንም የተፈጸመው የግፍ ግድያ በ 1980 ዓ.ም. በግንቦት ወር
ደጀና ውስጥ
ለውይይት ተሰብስበን አባይ ጸሃየ በድንገት “ ብፆት ግህንም ውስጥ የታሰሩ ስቪል እስረኞች አና ወታደሮች የሰው ዘር
በግፍ እየገደልን
ነው ...” ካለ በኋላ ሳያስበው ድንገት ከሕሊናው ገፍትሮ የወጣው ንግግሩ አስደነገጠው፤ ፊቱ ሁሉ ተለዋወጠ እና
ከስብሰባው ተነስቶ
ሄደ። ህ.ወ.ሓ.ት. የመላእክት ድርጅት ነው፤ በሰው ልጆች ላይ ግፍ አልፈጸምንም እያለን ያለው ብስራት አማረእየተከላከለለት ያለው
የፋሺስቶች ድርጅት በኔ ላይ የተደረገው የመግደል ሙከራ እና የአካል ማጉደል ወንጀል ብስራት እንደ ዲሞክራሲ
ይመለከተዋል።
የህ.ወ.ሓ. ት አረመኔ ስራ በተመለከተ ለወደፊቱ በዝርዝር የማቀርበው አሰቃቂ የወያኔ ህ.ወ.ሓ.ት. አመራር
የፈጸመው ደርግ በቀይ ሽብር
ያስደነገጣቸው ልብ ያልሰሩ ታዳጊ ወጣቶች ወደ ትግሉ ከተቀላቀሉ በኋላ በነዚህ ላይ አመራሩ ያሳለፈው (ከ 1970
ዓ.ም-1972 ዓ.ም)
የርሸና ውሳኔ አቀርባለሁ። እነኚህ የሞት ቅጣት የተወሰነባቸው እና እርምጃ የተወሰደባቸው ታጋዮች ዕድሜአቸው
ለአቅመ አዳም ያልደረሱ
የ 13 እና 14 ዕድሜ ወጣቶች ናቸው። ሁሉም የበረሃው ኑሮ መቋቋም አቅቷቸው፤ ወላጆቻቸው የናፈቁ ህጻናት
ነበሩ። ወላጆቻችን
ናፍቀውናል እና ወደ እየ ትውልድ ቀያችን መመለስ እንፈልጋለን የምትሉ አስታውቁን ይፈቀድላችኋል ብሎ
አመራሩ ካታለላቸው በኋላ፡እንሄዳለን ብለው እራሳቸውን ያጋለጡ ልጅ እግር ታጋዮች ከየቦታው ከሠራዊት
ማሰልጠኛ እና ከታጋይ ጋር የተቀላቀሉትን ሁሉ
እየተለቀሙ ተረሽነዋል። አረመኔው ወያኔ እነኚህ በጥይት ደብድቦ የገደላቸው ህጻናት “ ናብ እነይ ” ( ወደ እናቴ)
በሚል ቅጽል
ይጠራቸዋል።
የእነኚህ ወጣቶች ብዛት በጣም በርካታ ስለነበር፤
1 ኛ ፃኢ ሓለዋ ወያኔ ወዲ ሻምበል፤ ዘርኣይ ይሕደጐ እና ሙሉጌታ ዓለምሰገድ
2 ኛ ዓዲ በቕሊ 06 ዓለምሰገድ እይንቺ እና ተስፋይ ጡሩራ
3 ኛ ዓዲ ጨጓር 06 - ድልዊ- ብስራት አማረ - እና አሰፋ ጉሬዛ
4 ኛ ሱር 06 ጆቤ አበበ ተ/ ሃይማኖት እና ኣወተ ተስፋይ
6 ኛ ባኽላ 06 አበበ ዘሚካኤል፤ ሙሉጌታ ወዛም ( ማኢ ዶ አለክን)
በእነዚህ ስድስቱ ሓለዋ ወያኔ በወያኔ አመራር ትዕዛዝ እየተመሩ ተከፋፍለው የተረሻኞቹ ስም ዝርዝራቸውን
በመስጠት ለረሻኝ ክፍል
በመስጠት ህጻናቶቹ እንዲረሸኑ ተደርጓል። ይህ ጉድ የሚያወቁ አንዳንዶቹ ጆሯቸውን ደፍነው አውቀው እንዳላወቁ
ሆነው ውጭ አገር
የሚኖሩ አሉ።
ሁኔታው በጣም አስቀያሚ እርምጃ ስለነበር፤ በታጋዩ እና ህዝቡ መካከል መቃቃርን ስለፈጠረ አመራሮቹ ከዚህ
ተነስተው አባይ ጸሃየ ፤
ስብሓት ነጋ እና መለስ ዜናዊ በየቦታው ያሉት ታጋዮችን በማነጋገር ለድርጅቱ ህልውና ስንል እርምጃ ወስደንባቸዋል
እያሉ የታጋዩ ቅሬታለማቀዝቀዝ ሞከሩ። ለሕዝቡም በክፍሊ ሕዝቢ አማካይነት/ ሕዝብ ግንኙነት በኩል ተመሳሳይ ዘመቻ በማካሄድ
ለመሸፋፈን ሞከሩ።
የአሁኑ ጥያቄው የነዚህ ህጻናት ህይወት በዋናነት ተጠያቂው ማን ነው? አቅመ አዳም ያልደረሱ ህጻናት ለምን
እንዲረሸኑ ትዕዛዝ ተሰጠ?
ተጠያቂው አሁን በስልጣን ላይ የተቀመጠው ህ.ወ.ሓ. ት ነው። ይህ ወንጀለኛ እና ፋሺስታዊ ባሕሪይ ያለው ድርጅት
በማን አለብኝ
የሚፎልሉ ካድሬዎቹ ለነዚህ እና ለብዙ ሺህ ህይወት መቀጠፍ ተጠያቂዎች ናቸው። ጊዜው ይርዘም ይጠር በሕግ
መጠየቅ ይኖርባቸዋል።
ኢትዮጵያ በነፃነቷ ለዘላለም ትኑር
1
የብዙዎች አንደበት በተዘጋበት ፤ ፍርሀትና ልቅሶ በሰፈነበት ዘመን ብዕሩን
በማቅናት ያንን ቀውጢ ግዜ በብዕሩ የዳሰሰ ኢትዮጽያዊ ጸሀፊ ቢኖር በዓሉ
ግርማ ነው። ይህ ብዕር የዶለዶመው አንደበቱም የተዘጋው ሀሙስ የካቲት
24/1976 ዓ/ ም ከቀኑ 11:30 ከቤቱ ከወጣ በኋላ ተመልሶ ቤተሰቦቹን ማየት
ሲሳነው ሲሆን። ህይወቱ እንደ ብዕሩ ዛሬም ሚስጥር ሆናለች። በጊዜው የነበረው
መነግስት እጁ እንደሌለበት ለማሰተባበል የማፈላለጉ ስራ እንዲቀጠል ለይስሙላ
ቢያዝም ከመንግስት የተደረገ ምንም ጥረት አልነበረም። በቤተሰቦቹ ክትትል
በእለቱ ይነዳው የነበረው መኪና በደብረዘይት መንገድ ቆሞ የተገኘ ሲሆን ይህን
እውቅ ፀሀፊ ምን እንድበላው ዛሬም መልስ አለተገኘም። ከመጥፋቱ ሰባት ወራት
በፊት ከየመደርደርያው እየተለቀመ የተማገደው የደራሲው መጽሀፍ ፤
ከማስታወቂያ ሚኒስተር ስራው ተገልሎ እቤት እንዲቆይ መደረጉ ። አበዮቱን
መንጋጋ ውስጥ እኮነው የከተክተው የሚለውን ቅሬታ ከኮኔሬል መንግስቱ
መስማቱ የመሰወሩን ሚስጥር ግልጽ ያደርገዋለ።
በዓሉ መስከረም 10/1931 ዓ/ ም በኢሊባቡር ክፈለሀገር ክህንዳዊው አባቱ ና
በወቀቱ ሀበታም ከነበሩ ቤተሰቦች ከተወለዱ እናቱ ወ/ ሮያደኔ ቲባ በኢሊባቡር
ጠቅላይ ግዛት ሱጺ ቦሩ በምትባል አነስተኛ የገጠር መንደር የተወለደ ሶሆን አባቱ
ቤተሰባቸውን ወደ አዲስ አበባ ለማዛወር ሞክረው የእናቱ ቤተሰቦች
ባለመስማማታቸው ከእናቱ ጋር ኢልባቡር እንዲቀር ከአባቱም ጋር የጠበቀ
ገንኙነት አንዳይኖረው ሆኗል። በኢልባቡር ከአያቱ ጋር የጠበቀ ግንኙነትእንደነበረውና በጊዜው ስለነበሩት ምምህሩ በተደጋጋሚ ከማውራት ሌላ ስለ
ኢሊባቡር ህይወቱ ብዙም አያወራም ነበር። የአንደኛ ደረጃ ትምህርቱን እዚያው
በትውልድ ሀገሩ ሱጺ ከአጠናቀቀ በኋላ ወደ አዲስ አበባ በመመጣት በልዕለት
ዘነበወርቅ ትምህርትቤት ትምህርቱን መከታተል ጀመረ በጊዜው በሚሰጠው
ፈተና ክፍተኛ ውጤት በማግኘቱ በ 1943 ዓ/ ም ጀነራል ዊንጌት ትምህርትቤት
የመግባት ዕድል ለማግኘት ችሏል። በጀነራል ዊንጌት በጎበዝ ተማሪነቱ ፤
ተማሪዎችን ለአመጽ በማነሰሳት ችሎታው ሲታወቅ ስነጽሁፍን የሀይወት መርህ
ለማድረግ የመጀመሪያውን ጥሪ የተቀበለበት ግዜ እንደሆነ ይነገራል። በእዲስ
አበባ በነበረበት ግዜ አንደወላጅ የተንከባከቡትን የቅርብ ቤተሰብ ስም
በመውስድ በዓሉ ግርማ በሚለው መጠሪያ ይጠራ የጀመረው የኮሌጅ ተማሪ ሆኖ
ነበር።2
በዓሉ ግርማ በ 1954 ዓ/ ም ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በፖለቲካ ሳይንስና
በጆርናሊዝም የመጀመርያ ድግሪውን ሲያገኝ በትምህርት ላይ እያለ ለኢትዮጺያ
ሄራለድ ጋዜጣ በሪፖርተርነት እንዲሁም በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በጊዜው
ይታተም ለነበረው NEWS and VIEWS ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ሆኖ ሲያገለግል
የንጉሱን ሥርዓት የሚነቅፉ ጽሁፎችን በማቅረቡ ከመንግስት የተሰወረባቸው
ግዚያት ነበሩ። ትምህርቱን እንደጨረሰ የስኮላርሽብ እድል በማግኘቱ በፖለቲካ
ሳይንስ ና ጆርናሊዝም የማስተርስ ዲግሪውን East Lansing Michigan
ከሚገኘው በርክሊ ዩንቨርስቲ አግኝታል።
በስራ ዓለም
በ 1955 የዛሬይቱ ኢትዮጺያ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ
በ 1957 የመነነና የአዲስ ሪፖርት ምፅሄቶች ዋና አዘጋጅ
በ 1960
የኢትዮጺያን ሄራለድ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ
ከ 1962 – 1966 በጋዜጣው ህይወት ታሪክ ለመጀመርያና ለመጨረሻ ግዜ
ታማኝነት ባገኘው የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ
በ 1969 የማስታወቂያ ሚኒስተር ቋሚ ተጠሪ ሆኖ ሲያገለገል በአዲስ አበባ
ዩንቨርስቲ ተጋባዝ መምህር በመሆን በ creative writing ሙያ በርከት ያሉ
ባለሙያዎችን ለማፍራት ችሏል። በስራ ዓለም ተግባቢ ና ሰርቶ ማሰራት
የሚችል ፤ በሙያው የተመሰገነ እንደነበረ አብረውት የሰሩት ይናገራሉ።
ጋዜጦች ላይ በሚያቀርቡ ጸሁፎች የተናሳ የደሞዝ መቆረጥ ና ከስራ መባርር
የመሰሉ ችግሮችም ደርሰውበታል።ታዋቂው ጸሀፊ ስብሀት ገ/ እግዛብሄር በዓሉ ገፀባህሬዎቹን ከእግዛብሄር ይረክብና
ኑሮቸውን መጽሀፉ ውስጥ ያድርገዋል ይላል ፤ በርካታ የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ
ተማሪዎች በበአሉ ስንጽሁፍ ዙሪያ የመመረቂያ ጥናታዊ ጽሁፍ ሰርተዋል።
በርካታ ምሁራኖች ዘመናዊ ጸሀፊነቱንና ለሀቅ ሟች መሆኑን አስምረውበታል።
በዓሉ ግርማ በህይወት ዘመኑ በ 1962 ዓ/ ም ከአድማስ ባሻገርን በ 1966 ዓ/ም
የህሊና ደውልን በ 1972 ዓም የቀይ ኮኮብ ጥሪን ና ደራሲውን በ 1975 ዓም
ሀዲስንና ኦሮማይን እንዲሁም በየካቲት በሚለው የማስታወቂያ ሚኒስተር
ወርሀዊ መጽሄት ላይ የፍጻሜ መጀመሪያ የሚል ልብወልድ መጣጥፍ አቅርቧል።
የበዓሉ የስንጽሁፍ ስራዎች 3
1 የክርስቶስን የስብዕና ገጽታዎች በተወሰኑ መልኩ የሚያንጸባርቁ ፤
ዘላለማዊነት ያላቸው ገፀባህርያት በመጸሀፉ ውስጥ ይታያሉ ገፀባህሬዎቹ ለሰው
ልጆች አዛኝነት ርህሩርህነትን የሚያሳዩ ናቸው።
2 እራስን መገምገም ፤ተግባር ማከናወን፤ ውጤታማ ሆኖ መገኘት ፤ወቅታዊ
ማህበራዊ ና ፖለቲካዊ ችግሮችን ማንፀባረቅ የመጽሀፎቹ ተልኮች ናቸው።
3 ከወቅታዊ ሁኔታዎች ጋር የሚዛመዱ ፤ በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረቱ ፤
ታሪካዊነት ፤ ደፍርት ያላቸው ገፀባህርያትን ያዘሉ ሲሆኑ አፃፃፉ ፍቅርን፤ ሴራን
፤ ወሲበን አስታኮ የመተረክ ዘዴ ይታይበታል።
4 አንባቢያን ከገፀ ባህርያቱ ጋር በፍቅር እንዲወድቁ ፤ ከዕለት ተዕለት ኑራችን
ጋር የሚመሳሰል ትዝታን የመፍጠር ችሎታ ያላቸው ገጸ ባህርያት የታየሉ
5 በየጊዜው የነበሩ ግራ አዝማሚያዎችን ፤ ከውጪ የሚመጡ አሰተሳሰቦች
ለኢትዮጺያ እንደ ማያስፈልጓት ፤ የግለሰብ ነፃነትን አስፈላጊነተን አጥብቆ
ይከራከራል።
6 በጋዜጠኞች ፤በጻሀፊያን የሚደርሰውን ተጽዕኖን በማጋለጥ የፕሬስ ነፃነት
አሰፈላጊነትን አጉለቶ ያሳያል።
7 በሴት እህቶቻችን ላይ የሚደርሰውን በደል ፤ ማሀበረሰቡ ለሴቶች ያለውን
የተዛባ አዝማሚያ የሴቶች እኩለነትና የባህል ታሀድሶ አስፈላጊነት አጥብቆ
በመከራከር በሁሉም መጽሀፎቸ የዋና ገጸባህረተያቱ ታሪክ በማድርግ ችግሩ
ጎልቶ እንዲወጣ ታለቅ ተዋጾ አበርክቷል በአድማስ በሻገር ሉሊት፤ በህሊና
ደውል ሽታዮ፤በደራሲው ዕጌ፤ የቀይኮከብ ጥሬ ፍኖት እነዲሁም በኦሮማይ
ፍያሜታ ክብረ ንዕህናቸው በሀይል የተገፈፉ በደረሰባቸው በድል ምክንያት
ህይወታቸው ከሀዲድ እንደወጣ በማሳይት ማህበረሰቡን ለማስተማር ችሏል።
8- በአብዮቱ ወቅት የታዩትን ኢሰባዊ ድርጊቶች በማመዝግብ በወቅቱለመህበረሰቡ ያቀረቡ ፤ በታሪክነታቸው ፤ በትምህርትነታቸው ለማሰቀምጥ
የቻሉ ታሪካዊ ስራዎች ናቸው።
ከእድማስ ባሻገር 4
የመጀመሪያው የደራሲ በዓሉ ግርማ የህትማት ሥራ ሲሆን ስምንት ግዜ ታተሞ
ለመሽጥ ሲችል።እራሱን አንድ ቀን ለመግለጽ በሚዋትተው በዋናው ገፀባህሬ
አበራ ወርቁ ፤ ከውስጡ ያለውን ብርሀን ለማየት እንዲችል አበራን
በሚጎተጉተው ሀይለማሪያም እንዲሁም በዘራቸው በማንነታቸው የሚኮሩት ይሁነ
እንጂ የሚፈልጉትን ካዲሱ ትውልድ
በሚያውቁት ወንደሙ አቶ አባተ ገፀባህርያት ላይ ያነጣጠረውና በጊዜው
የነበረው ወጣት ምሁር እራሱን ለትልቅ ሀላፊንት ያጨ ቢሆንም ከወላጆች ፤
ከመንግስት ትከሻ ላይ ተንጠልጥሎ ከመውሰድ በስተቀር መልሶ የተካው ምንም
እንደሌለ ትውልዱ ያለበትን ችግር ጠነቅቆ የማያውቅ ችሎታውንና ህልሙን
ያለፈተነ መሆኑን ። የወደፊቱን ባለቅኔ ፤ ደራሲ ፤ ሰዓሊ ፤ የጥብብ ጎህ ቀዳጅ
ሊሆን የሚችል ትውልድ ሀላፊነቱን ሊወጣ ያልቻለበት ምክንያቶች ከምሁሩ ፤
ምሁሩን ካፈራው ማህበረሰብ ፤ ወይስ ምሁሩ አልፈው ከመጣው ተቋም በማለት
በውቅቱ ሀገሪቱ ያፈራቻቸው ምሁራን አቅጣጫ ሊመረመር እንደሚገባው
አጽንቶ ይክራከራል።
“ በጧት መጥቼ በዚህ ወንበር ላይ ስጎለት ራሴን የምመለከተው የበሰበሰ
እንቁላል ላይ የተቀመጠች ዶሮ አድርጌ ነው የምቆጥረው ነገር ግን ግማቱ
አይሰማኝም። ” በማለት የሚናገረው አባራ የደራሲ ባዓሉን መጽሀፍ ወና
መልክት ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።
የህሊና ደውል
የኢትዮጺያ ሰረየት የሚሰራ እጅ ነው ። በባድ ሀሳብ ላይ የተመሰረተ
መሻሻል ትርጉም አይኖረውም በማለት በኢሊባቡር መቱ አቅራቢያ
የምትገኘውን የሱጺ በሮን ከተማ መልካ ምድር ፤ በ 1966 ዓም የታየውን ድርቅ
፤ በማህበረሰቡ የዕለት ተዕለት ኑሮ ላይ ይታይ የነበረውን የከፋ ህይወት እየተረከ
ህይወቱን ፤ ፍላጎቱን ና የዘመኑን ትውልድ ፍልስፍና በመተው በውቅቱ
የዩንቨርስቲ ትምህርቱን አቋርጦ ትምህርት የህብረተሰቡ ጉዳይ ነው
በህብረተሰቡ የሚካሄዱ ትምህርት ቤቶች ናቸው የሚያስፈልጉት በማለት
ትምህርት ቤት ለመስራት ሀዋርያ ስለ ሆነው መምህር አዲስ የሚተርከው የህሊና
ደውል በጊዜው ይታይ የነበረውን ፖለቲካዊ ውዝንብር በግልጽ በማጋለጥ
ሀገሪቱን አስተሳስሮ ያቆየው ገመድ እየመነመነ መሄዱን ይህን ገመድ እንደገናለማጠናከር ከባዳን የፖለቲካ ፍልስፍና ፤ከጥቂት ሰዋች ጥቅምና ፍላጎት ፤
ከጎሳና ከሀይማኖት በላይ ከኢትዮጺያን ባህሬ ልምድ፤ ባህልና ኑሮ የመነጨ
ተነጥሮ የወጣ የፖለቲካ ፍልስፍና አይዲዮለጂ መመስረት አለበት ብሎ
በአጽኖት የሚከራከር ሲሆን ሀገሪቱም ለውጥ እንደሚያስፈልጋት የለውጥ ህግ 5
ከተገደበ ወድ ኩሬነት ተለውጦ ጤናማ አይሆንም የሚለውን የባዓሉን ብዕር ዛሬ
ዞር ብሎ ላጤነውየጻሀፊውን ብስልት መለካት ይችላል። ይህ መጽሀፍ ግለሰቦች
በማህብረሰቡ ውስጥ የሚጫወቱት ሚና መልካም ነገር ለመስራት ምን ያህል
አስተዋጾ እንዳለው መምህር አዲስና ፊታውራሪ ተካ የነበረወን ችግር ሁሉ
ተቋቁመው ለሱጺ በሮን ህጻናት ትምህርት ቤት መስራታቸው ይቸላል የሚለውን
የዘመኑን አባባል በዓሉ ቀደም ብሎ እንደገለጸው
እንድናጤን ያደርገናል ። በዚህ መጽሀፍ አብዛኞቹ ገፀባህርያቱ/ የፍቅረ
ሰባኪዋች ሲሆኑ ደራሲው ሰዋች ከዓላማችው ጋር በፍቅር ሲወድቁ ህይወት የተለየ
ትርጉም እንደሚኖራት በሚቀጥለው ሁኔታ ገልዖታል።
“ ያለፍቅር ህይወት ትርጉም የላትም ህልውናዋ ባዶ ፤ የሚጮህ ናሳ ወይም
የሚንሿሿል ፀናጽል ትሆናለች ያለፍቅር ብሔራዊ አንድነት ትርጉም የለውም
ፍቅር እግዜር ነው። ፍቅር ከልባችን በሚመነጭበት ወቅት እያንዳንዳችን
እግዜር እንሆናለን ፍቅር እግዛብሔር ነው። ”
የቀይ ኮከብ ጥሪ
የፊውዳሉ ስርዕት ቅሪት በሆኑት በፊታውራሪ ጉልላትና በባለቤታቸው ወሮ
አምሳለ በኢህአፓ አባላት ልጆቻቸው በሂሩትና ተሰማ የጊዜው ሁኔታ ጭራሽ
ባልጣመው ጋዜጠኛውና ቢሮክራቱ የወ/ ሮ እምሳለ ወንድም ጌታቸው
በፊታውራሪ ቤት ባደገውና የቀይ ኮከብ ጥሪ በተቀበለው ደርቤ ታሪክ ዙሪያ
በጊዜው የነበረውን የማህበረሰቡን ምስቅልቅል አመለካከት ልዩነት በማውሳት
የሚተርክው የቀይ ኮከብ ጥሪ የበዓሉ የድህረ አብዮት የበኩር ልጅ ሲሆን በቀይ
ሽብር ዘመን የነበረውን ቀውጢ ህይወት ቁልጭ አድርጎ ያስቀመጠ ነው። ግዜው
ምቀኝነት የግል ፍላጎትን በመድብ ትግሉ እያስታከኩ የሚያወናብዱበት
እንደነበረ በጊዜው የውይይት ክበብ አባሎች ስራውንም ስልጣኑንም በመያዝ
ሀገሪቱን ወደ ማትወጣበት ችግር እንደከተቱ የቀበሌ አብዮት ጥበቃዎች ፍርዱን
በእጃቸው በመያዝ ኢድህ ፤ አናርኪስት በማለት ብዙ እናቶችን ፤ እህቶችን
ደፍረው ፤ አይናቸው አወጥተው ፤ ጡታቸውን ቆርጠው፤ የህዝቡን ልጆች
ካለርህራሄ አስቃይተው የኢሀፓን ጋዜጣ እያስታቀፉ በየመንገዱ
እንደሚወረውሩ። በተለይ በመዲናዋሀአዲስ አበባ የሰላም እንቅልፍ የሚተኙየታደሉባት ሀዘን የወረሳት ከተማ እንደነበረች ቀይ ሽብር የተፋፋመበት ሬሳ
በየመንገዱ ዳር ወድቆ ሲታይ ልጆቸቸው የጠፋባቸው ቤተሰቦች ሬሳ በማገላበጥ
ለጆቻቸውን ሲፈልጉ መሰተዎሉን ፤ ወታደሮች በቀሚ ተጠሪ በመባለው 6
ጂፓቸው በመሆን በአዲስ አበባን ህዝብ ላይ ፍርሀት ማንገሰቸውን ያተተ ታሪካዊ
መጽሀፍ ነው።
በወቅቱ በሀገሪቱን በበቀሉት የተላያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች መክንያት
የተፈጠረው ሽኩቻ ተራ ግድያን በመፍጠር በሀገሪቱ ላይ የማየጠፋ እሳት
መጫሩን የፖለቲካ ድርጀቶች የወጣቱን ጠንካራ መንፈስና ድርጅታዊ
ዲሲፒሊን ለሀገር በማይጠቅም ርዮተዓለም ከማበከን በሀገር ላይ እንዲውል
ቢያደርጉት ስንት መልካም ስራ ሊሰራ እንደሚችል እያተተ በጊዘው የነበረው
ህይወት የደንቁርን ዓለም እንደነበር መጽሀፉ ያመላክታል።
ሀዲስ
በህሊና ደውል የኢትዮጸያ ስሬት የሚሰራ እጅ ነው በማለት የተግባር ህይወቱን
ያሳየው ሀዲስን በዓሉ ግርማ በጣም በሚጥም ያጻጻፍ ስልትና ለአንባቢ በሚቀልና
አቀራረብ ተንታኝ በሆነ መልኩ እዲስ በሚለው መፅሀፉ ህየወቱን የብዙሀን ወኪል
አድርጐ እንዲታይ አድርጎታል ። ሀዲስ ስራ ለመፈለግ በሚያደርገው ጥረት፤
ምልካም ነገር ለመስራት ሲፍጨረጨር ከቢሮክራሲ ጋር የሚያደርገው እሰጣ ገባ
፤ግልፅ፤ የዋህና ደፋርነቱ የአንባቢያንን አይን የሚስብና በዓይነ ህሊናችን ብዙ
ሀዲሶችን እንድንቃኝ ያደርገናል።የትምህርት ዓላማ መሆን ያለበት ትምህርትን
ማዳረስ ሳይሆን ሀገሪቱን ሊመሩ የሚችሉ ጥቂት ጥራት ያላቸው ምሁራንን
ማፍራት ነው ። ህሊና ሀይማኖት የሚለት ዝባዝንኬዎች ለእድገት ጠንቅ ናቸው
።ማህበራዊ ሀበት ክፍፍል ሶሻሊስታዊ አስተያየት ነው በማለት በድርጊቱም ሆነ
ባስተሳሰቡ ከሀዲስ የተላየው ታፈስና ሀዲስ የሚያደርጉት የወቅቱ የሀሳብ ልዩነት
በውቅቱ ብቅብቅ ያለው ካፒታላዊ ስረአት አቀንቀኝ ክፍል የነበረውን የተሳሳተና
ከሀገሪቱ ሁኔታ ጋር የማይሄድ አሰተሳሰብ ቀልጥ አድረጎ የሚሳይ አቀራረብ
ነው።
ደራሲው
የደራሲያንና የተደራሲያንን ሙግት በሰፊው የሚታይበት ሲሆን ደራሲው
እውነተኛ ደራሲ ለመሆን ያለውን ጥብቅ ፍላጎት
“ ከምፈጥረው ገፀ ባህርያት አጥብቄ የምጠብቀው ማህበራዊ ድፍረት፤ ትህትና ፤
ፍቅር ፤ ሀቀኝነት፤ ቀጥተኛ መሰዋትነት በእኔ ባህሬ ውስጥ የት አለ ?’’7
“ መጻፍ አልቻልኩም ሀቁ ይህ አይደለም ሀቁን ክእራሴ እደብቀዋለው ፤ መጻፍአልቻልኩም ጊዜዬን በከንቱ ነው የማጠፈው የምለው ነገር የለኝም ቢናረኝም ምን
እንደሆነ አላውቅም ባውቅም በቃላት ልገልጸው አልቻልኩም ቃላት መግለፅ
ያለባቸውን አይገልፁም ያሾፋሉ። ” እያለ ከእራሱ ጋር የከፈተው ጦርነት ዘመኑ
ምን ያህል የፍርሀት ዘመን እንደነበር የሚያሳይ ሲሆን በወቅቱ በሀገሪቱ ወስጥ
የነበረውን ፖለቲካዊ ቅራኔ
“ ሱሪ ባንገት አውልቅ ምርት! ምርት! አረነጓዴ ዘመቻ ውይይት ክብብ፤
ውግዘት ፤እርግማን፤ መኮነን፤መጠቆም ፤ ማጋለጥ ፤ መዋጮ ለእናት ሀገር ጥሪ
፤ ለመልሶ ማቋቋም ” በሚመስል አገላለጽ የገለጸው ሲሆን የተረት ስፈርን
ነዋሪዎች የዕለት ተዕለት ኑሮ በከተማ ቤት አዋጅ ምክንያት የተፈጠረውን ችግር
በመዘርዘር በሀገሪቱ የሰፈነውን ማህበራዊ ውድቀት ያወጋበት መፅሀፍ ነው።
ደራሲው
1 - በጋሀዱ ዓለመና በተስፋ ዓለም መካከል ያለውን ልዩነት አጉልቶ የሚያሳይ
2- ሰፊ ያስተሳሰብ ለዩነት በማህበረሰቡ ውስጥ እንዳለና መንኛውም ለውጥ ከዚህ
አስታሳሰብ መመንጨት እንዳለበት የሚጠቁም
3- የሀገሪቱን የኑሮንና የኢኮኖሚ ውድቀት የማህበረሰቡን የዕለት ተዕለት ህይወት
በመኖር እንድናየው ያደረገበት
4- በሀገሪቱ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚ አቅጣጫ ላይ የማረምና የማስተማር አቀራረብ
የሚታይበት
5- በጊዜው የነበረው ስርዕት ከእራሱ አስተሳሰብ ጋር እንደሚጋጭ ያጋለጠበት
7 የመናገር ፤ የመጻፍ ፤ የማንበብ ነዓነት ከግል ነፃነት እንዴት እንደሚነፃፀር
ያስተማረበትና በወቅቱ ጸሀፊያን ያለባቸውን ችግሮች በሰፊው የሚያትትበት
ነው።
ኦሮማይ
ንግግር ፤ ንግግር ብዙ ንግገር ትንሽ ስራ ግምገማ ፤ ግምገማ ብዙ ግምገማ ትንሽ
ውጤት ፤ መፈክር ፤መፈክር 8
ነጋ ጠባ ዘመቻ እድገት በህብረት ብሎ ዘመቻ ፤ ለጦርነት ዘመቻ ፤ የኢኮኖሚ
ግንባታ ዘመቻ ፤ ማሀይምነት ለማጥፋት ዘመቻ ፤ የቁጥጥር ዘመቻ ፤ አሁን
ደግሞ የኤርትራን ችግር ለመፍታት ዘመቻ
ነጋ ጠባ ስብሰባ ፤ ጠዋት ስብሰባ ፤ ማታ ስብሰባ ፤ የማያቋርጥ የስብሰባ ህይወት
የኢትዮጺያ ችግር ሁሉ ባአዋጅና በዘመቻ እንደ በጋ ጉም በኖ የሚጠፋ
ይምስላቸዋል መሰረታዊ ችግራችን የአይምሮ ድህነት መሆኑን ያዋጅ ፤
የማጠናቀሪያ አዋጅ ጋጋታ ፤ ዘመቻ ብሎ ጭጭታ ትርምስ መተራመስተተራመሶ መሞት በማለት በጊዜው በጥናትና በዝግጅት ላይ ያልተመሰረተው
የሀገሪቱ ሀብት በተገበረበት በቀይ ኮከብ ዘመቻ የማስታወቂያ ሚኒስትሩ ተወካይ
ፀጋዬ ሀይለማሪያም ታሪክ ላይ ያነጣጠረውና የታሪኩ ተራኪ እራሱ ደራሲው
መሆኑን በየምዕራፉ እያስተዋወቀ በደራሲው በእውን የታየው ፤ የተደረሰውና
የተተረከው ኦሮማይ በኢትዮጺያ ታሪክ ታሪካዊና ህይወትን መሳይ ድንቅ ነገር
የተሰዋበት ድንቅ መዕሀፍ ነው። በዚህ መፅሀፍ በጊዜው የነበረውን የኤርትራን
ችግር ፤ሴቶችን በመድፈር፤ ካለመንም ፍርድ የሞት ቅጣት በመፈፀም ፤
ወጣቱን በማስበርገግ የብህራዊ ጦር ፤ የ 15 ኛ ብርጌድ ፤ ህብረት ዕዝ ፤ ከደርግ
ምርመራ አፋኝ ጓድ ፤ የህዝብ ድርጅት ጊዚያዊ ጽህፈት ቤት የመሳሰሉ
ቡድኖች ለችግሩ መባባስ ምክንያት እንደሆኑ በግልፅ ያስቀመጠ ሲሆን
ውታደሩ ከአመራሩ በተለየ መልኩ ሀገሩን የሚወድ ለሀገሩም የተሰዋ ቢሆንም
ጦርነቱ ፖለቲካዊ መፍትሄ ያልተፈለገበትና አዝማቾቹም ከሀገራቸው ይልቅ
እራሳቸውን የሚወዱ ችሎታውና ብቃት የሌላቸው ለጦርነቱም የነበራቸው
አመለካከት በጣም የቀለለ የኤርትራም ህዝብ በባለስልጣኖች በደረሰበት ስቃይ
ከሻቢያ ጋር ለማበር መገደዱን ሀገሪቱም የማትችለው ጦርነት ላይ መዘፈቋን
አስቀምጧል።
የወቅቱን ባለስልጣኖች በገፀባህሬ መልክ በመሳል እውነተኛ ማንነታቸውን ፤
ልግል ጥቀማቸው የሚያደርጉትን መሯሯጥ ፤ ለስልጣን ያላቸውን ጥም ለጦርነት
ሳይሆን ባአስመራ ሴቶች ላይ ለመዝመት የመጡ ዝሙተኞች እንደነበሩ
በድፍረት ፅፎታል።
የፍጻሜ መጅምሪያ
በበዓሉ ግርማ በግዜው በማስታወቂያ ሚንስተር ይታተም በነበርው የካቲት
ምዕሄት ላይ ብቸኛ የታተም አንስተኛ መጻጻፍ ሲሆን የታሪኩ ገፀባህሬ ህሊና 9
የሚባል ሰው ሲሆን ህሊና ጠጪና ስለ ዕውነት ና ሀቀ ኝነት ለመጸፍ ከእራሱ ጋር
በሚያደርገው ትግል ስለነበረው ተስፋና ሰስለነበረበት ፍርሀትነና በጊዜው ሰለ
መሰወሩ በኋላም ተመልሰው የሚያደርጉትን ጭውወት የሚተርክ ሲሆን መዕሀፉ
በዓሉ ግርማ ክህሊናው ጋር ተመልሶ እንደተገናኘና ከህሊናው ጋር በመታረቁ
መሰወሩንና የሚደርስበትን ለመቀበል መዘጋጀቱን የነገረን ዘዴ ሊሆን
እንደሚችል ጽሁፉን ያነበቡ ሁሉ ይገምታሉ።
በአድማስ ባሻገር
ጊዜው አላለፈም ይህይወትን ጥሪን ካወቅ ዘንድ ላአንድ ቀን እንኳን እራስህን
ግልጽበህልና ደውል
ስለችግርና ስለ ብቸኝነት ለመዝፍን ፍላጎት የለኝም መጻፍ የምፈልገው ስለ
ዓለም ውበትና ስለሰው ተፈጥሮ መሰረታዊ ጥሩነት እንዲሁም ሰው በራሱ የራሱን
ደህንነት እንዳያገኝ ስለሚያደናቅፉት አካባቢዎች ነው።
በቀይ ኮከብ ጥሪ
ያለ ድርስት ሌላ ህይወት የለኝም ምኞቴ በድርሰት ለሰው ልጅ ደስታን
ለማስገኝት ነበር ግን ለሰው ልጅ ደስታን ለመስጠት አልቻልኩም ለራሴም ደስታ
አላገኘሁም ስለዚህ የመኖር ትርጉሙ አልታየኝም ባዶነት ይሰማኛል ባዶነትን
ፍጹም የሚያደርገው ደግሞ ሞት ነው ፍጹም መሆን አለበኝ
በሀዲስ
እኔ የምወደው በሰው ልብ ተሰፋ ፍቅርና ቆራጥነት የሚያጠናቅር ውበት ያለው
ቅኔ ነው።
በደራሲው
እኔ የምጽፈው ስለ ልበ ሙሉነት ስለ ድፍረት ነው 10
ድፍረት ለሌለው ብዕር ወረቀት ባታበላሹ ይሻላል
የሰው አካለና ነፈስ አንደ ስለሆነ የሚጸድቀውም የሚኮነነውም በራሱ ልብ ውስጥ
ነው።
በኦሮማይ
የሚሞትበትን የሚያውቅ ማን አለ? በነፃነት ኖሮ በነፃነት ሞሞት የሻላል።
ብዕሩ ዕውነትን ለመግለፅ በትግል ላይ እንደነበረች ፤ ስሜቱ ሰው ከማንም በላይ
ክቡር መሆኑን እንደገለጸች ፤ ምኞቱ በብዕሩ ለወገኖቹ ደስታን መቸር መሆኑን
፤የድርሰት ፍቅሩ የልክፍት ያህል ከድርስት እንደተቃራኘ መኖሩን ደፋርና
አዋቂ ታላቅ የስንዕሁፍ ሰው እንደነበረ በፁሁፎቹ ከእውነትና ክድርሰት ሊለየው
የሚችል ሞት ብቻ እንደነበር ይህንንም ለመቀበል ዝግጁ መሆኑን ብብዕር
ውጤቶቹ ቁልጭ አድርጎ ያሳየን ታዋቂው ደራሲ ዛሬ በህይወት ቢኖር ብዙ
ስራዎችን ሊያካፍለን ይችል የነበረ ሲሆን
የበርካታ ሰማዕታት አሟሟት ሚስጥር ሲገለጽ
የንጉሱ አዕም ከኮ/ መንግስቱ ሐ/ ማርያም ቢሮ ስር ተቆፍሮ ሲወጣ
የ 60 ዋቹ የንጉሱ ባለስልጣኖች አፅም ከአዲሰ አበባ ከርቸሌ በፍለጋ ሲለቀም
የእነ አቡነ ቴዎፋለዎስ አፅም ክልዑል አስራተ ካሳ መኖሪያ ግቢ ውስጥ በቁፋሮ
ሲገኝ
በዓሉ ግርማ የት ገባበመጭረሻ ለበርካታ ደራሲ በዓሉ ግርማን ለበርካታ ዓመታት መለስ ያላገኙትን
ቤተሰቦቹን በተለይም ባሌቤቱንና ልጆቹን ለአንድ ደቂቃ በህሊና ጸሎት
እንድናስባቸው እንጠይቃለን
TEKLEHAIMANOT GEBREMEDHIN EMBAYE
JOURNALISM STUDENT SECOND YEAR IN BAHIR DAR
UNIVERSITY -
ፐርዝ አውስትራሊያጥቅምት 4 ቀን 2011 (እ.ኤ.አ.)

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ