2017 ኤፕሪል 26, ረቡዕ

ሶስት የአፍሪካ አገራት የመጀመሪያውን የወባ ክትባት ሊያገኙ ነው

tgonorham
tgonorham
ብጋዜጠኛ ተክለሃይማኖት ገብረመድህን ካብ ባህር ዳር ዩኒቨርሲትይ

ሶስት የአፍሪካ አገራት የመጀመሪያውን የወባ ክትባት ሊያገኙ ነው

teklehaimanot gebremedhin
tgonorham
ሚያዝያ 16፣ 2009
የአለም ጤና ድርጅት የመጀመሪያ የሆነውን የወባ በሽታ መከላከያ ክትባትን በሶስት የአፍሪካ አገራት ላይ በቀጣዩ አመት ጥቅም ሊያውል ነው።
ኬንያ፣ጋናና ማላዊ  ናቸው ለመጀመሪያ  ጊዜ  ጥቅም ላይ እንዲውል ይፋ  የሆነውን የወባ በሽታ ክትባት የሚያስተዋውቁት።
አር ቲ ኤስ የተሰኘው የወባ በሽታ ክትባት   የሰውነት በሽታን  የመከላከል  አቅም በወባ  ትንኝ አማካኝነት የሚከሰተውን የወባ በሽታ እንዴት አድርጎ ማጥቃት እንደሚችል ልምምድ የሚሰጥ ነው ተብሏል።
የአለም ጤና  ድርጅት  ክትባቱ በአስር ሺዎች የሚቆጠርን ህይወት የማዳን አቅም እንዳለው አመልክቷል።
teklehaimanot gebremedhin
tgonorham
ይሁንእንጂ  ክትባቱን በድሃ አገራት መጠቀም ከአቅም አንፃር የሚቻል መሆን አለመሆኑን  የሚገልፅ ነገር አለመኖሩን ቢቢሲ አመልክቷል።
ክትባቱ ስኬታማ እንዲሆን በየወሩ በተከታታይ  ለሶስት ጊዜ ያህልና ለአራተኛ ጊዜ ደግሞ ከ18 ወራት በኃላ  በጥብቅ ክትትል መሰጠት አለበት።
tgonorham
tgonorham
ለዚህም ነው የአለም ጤና ድርጅት ሶስቱን የአፍሪካ አገራት በሙከራ ደረጃ  መርጦ በቀጣዩ የአውሮፓዊያን ዓመት ወደ ስራ  እንደሚገባ ያስታወቀው።
በአለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ  ዳይሬክተር  ዶ/ር ማትሺዶ ሞቲ እንደተናገሩት መልካም ዜና የሆነውን የወባ  በሽታ ክትባት በአገራቱ  ላይ የሙከራ  ውጤቱን  በማየት በቀጣይ በስፋት ለመግባት ያስችላል ብለዋል።  
ቢቢሲ እንደዘገበው በሙከራ ፕሮጀክቱ  750 ሺህ ህፃናት የሚካተቱ ይሆናል።




tgonorham
ተክለሃይማኖት ገብረመድህን

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ