2017 ኤፕሪል 26, ረቡዕ

TG Onorham

የፍቅር ሂሣብ



አለም ሂሣብ ሰርታ፣
ፍቅር ስጦታ፣
ባላንስ አልመጣ አለ፣
የወጣው አየለ፣
ያልተከፈለ አለ፡፡

በልቶ እንደቆሎ፣
ያልሰጠ በቶሎ፣
ፍቅርን አታለለ፣
ከአለም አጐደለ፡፡

የፍቅርን ዝውውር፣
አደረገ እንዲያጥር፣
ላለም የሾህ አጥር፣
በመሃል ጥርጥር
በጥይት ማበጠር፣
ደግሞ በድርድር፣
በነገር መካረር፡፡
ባካችሁ ልባችሁን፣
አንዴ ፈትሹልን፣
ባላንሱ ይምጣልን፡፡
































ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ