2017 ሜይ 17, ረቡዕ

ስለአንድ ጉዳይ ከመጠን በላይ ማሰብ በ3 መንገዶች በሰዎች ላይ ጉዳት ያስከትላል

ስለአንድ ጉዳይ ከመጠን በላይ ማሰብ በ3 መንገዶች በሰዎች ላይ ጉዳት ያስከትላል

ስለ አንድ ጉዳይ አብዝቶ መጨነቅ ወይም ከመጠን በላይ ማሰብ የመፍትሔ ሀሳብ እንደማይሆን የስነልቦና ባለሙያዎች ይናገራሉ።
ሰዎች በማንኛውም ጊዜ ስላጠፉት ጥፋት ወይም ስላልተሳካላቸው ነገር አብዝተው ሊጨነቁ ይችላሉ።

ጥፋቱን ለምን ሰራሁት ወይም ደግሞ ያልተሳካውን ነገር እንዴት ነው የማሳካው በሚል መብሰልሰል ውስጥ የመግባት እድልም ይኖራቸዋል።

በእርግጥ ማንኛውም ሰው አልፎ አልፎ ከመጠን በላይ የሆነ ሀሳብ ውስጥ ሊገባ ይችላል።

በርካታ በስነ አዕምሮ ዙሪያ የተደረጉ የስነልቦና ጥናቶች፥ ከመጠን በላይ በአንድ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ማሰብ እና አብዝቶ መጨነቅ የጤና መቃወስን ያከትላል ይላሉ።

በተለይም ከመጠን በላይ ማሰብ ከዚህ ቀጥሎ በተዘረዘሩት ሶስት መንገዶች በሰዎች ላይ ጉዳት እንደሚያስከትል ተጠቁሟል።

1. ለአዕምሮ ህመም የመጋለጥ እድልን ይጨምራል

በጆርናል ኦፍ አብኖርማል ሳይኮሎጂ ላይ የሰፈረ እና በፈረንጆች 2013 የተሰራ አንድ ጥናት ሰዎች በስህተቶቻቸው እና በሚያጋጥሟቸው ችግሮች

ዙሪያ አብዝተው የሚያስቡ ወይም የሚጨነቁ ከሆነ ለአዕምሮ መቃወስ የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ እንደሚሆን ያሳያል።

ከመጠን በላይ ማሰብም ለማያቋርጥ መብሰልሰል በመዳረግ አዕምሮ ተገቢውን ስራ እንዳይሰራ ያውከዋል ነው የሚለው ጥናቱ።
2. በችግር አፈታት ሂደት ላይ እንቅፋት ይፈጥራል

ጥናቶች አብዝተው የሚያስቡ ሰዎች ችግሮቻቸውን በአዕምሯቸው ውስጥ በማመላለስ መፍትሔ ያገኙ ሊመስላቸው ይችላል።

ሆኖም ለችግሩ መፍትሔ ለማምጣት በሚል ሰበብ አብዝቶ መጨነቅ እና ከመጠን በላይ ማሰብ ለአካላዊ መተሳሰር እና ሌላ ስራን ለመስራት ዝግጁ አለመሆንን ያስከትላል።

ይህም ሲሆን ደግሞ ችግር የመፍታት ሂደቱ ይስተጓላል፤ ቀሪው የህይወት ምዕራፍም ተስፋ እንዳይኖረው ሌላ እንቅፋት ይፈጥራል ነው የተባለው፡፡

ምክንያቱም አብዝቶ ማሰብ በችግሩ ላይ እንጅ በመፍትሔው ላይ ለማተኮር እድል ስለማይሰጥ ነው፡፡

3. የእንቅልፍ መቃወስን ያስከትላል

ሰዎች በአንድ ጉዳይ ላይ ከመጠን በላይ የሚያስቡ ከሆነ ብዙ ጊዜ እንቅልፍ አይተኙም፤ ቢተኙም እንኳ የተራጋጋ እንቅል አይወስዳቸውም፡፡

ጥናቶች ከመጠን በላይ ማሰብ እና በአንድ ርዕሰ ጉዳይ ላይ አብዝቶ መጨነቅ፥ ሰዎች በቂ እረፍት እንዳያደርጉና የእንቅልፍ እጥረት እንዲጋጥማቸው ያደርጋል ነው የሚሉት።

የእንቅልፍ እጥረቱ የሚከሰተው በአዕምሮ ላይ በሚፈጠረው መጨናነቅ ምክንያት ነው።

የሆነው ሆኖ ከመጠን ያለፈ ሀሳብን ለመግታት አዳዲስ ሀሳቦችን ማፍለቅ፣ በዕቅድ መመራት እና ላለፈ ነገር አብዝቶ አለመጨነቅ ወሳኝ ናቸው ተብሏል።
ምንጭ፡-ሳይኮሎጂ ቱዴይ(በሪፖርተር ተክለሃይማኖት ገብረመድህን)
ከባህር ዳር TGOnorham

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ