2017 ሜይ 23, ማክሰኞ

እኛ ባቡርና አዉሮፕላን ማረፊያ ሳይሆን የጠጠር መንገድ እንኩዋን ማግኘት አልቻልነም፡፡ መቀሌ ህወሓት ወጣቶች ሊግ


መንገድ ያጣው መንገደኛ ህዝብ ትግራይ Image result for tplf

ከዚህ በታች የተዘረዘሩት በባለፉት 26 አመታት በትግራይ  ሊሰሩ በጀት ተይዞላቸዉ፤የመሰረት ድንጋይ ተቀምጦላቸዉ፤ተጀምረዉ የዉሃ ሽታ ከሆኑት መንገዶች ከፊሎ ናቸው። እኛ ባቡርና አዉሮፕላን ማረፊያ ሳይሆን የጠጠር መንገድ እንኩዋን ማግኘት አልቻልነም፡፡
1. ከሽረ - ማይ ፀብር -ደደቢት - ሁለት ግዜ የዉጭ እርዳታ ተገኝቶለት ያልተሰራ ገንዘቡም የት እንደገባ ያልታወቀ በሚዲያ በተደጋጋሚ ተነግሮለት የቀረ
2. ከዕዳጋዓርቢ  -ዕዳጋ ሐሙስ -ነበለት ፡ በተደጋጋሚ ቃል እየተገባና እየተለካ የቀረ
3. ከነበለት -ሐዉዜን ፡ ቃል ተገብቶ የቀረ
4. በገለበዳ -ሃገረ ሰላም -ተምብየን  ከዛሬ 20 አመት ጀምሮ ቃል ለህብረተሰቡ በየ 5 አመቱ እየተገባ የቀር
5. ከባድመ -ሰምበል -ዋዕላ ንህቢ -ሸራሮ ፤ ከሶሰት አመት በፊት ተጀምሮ የቀረ
6. ከነበለት -አዝመራ -አረጊት (በዓረና ምእራባዊ በኩል) በ2002 ምርጫ ስራ ተጀምሮ ምርጫዉ እንዳለቀ ስራዉ የቆመ
7. ከነበለት -አሕፎሮም  ከሃያ አመት በሁዋላ የተጀመር አሁን እጅግ ጥራቱ በዎረደ መልኩ እየተሰራ ያለ
8. ከአሕፎሮም -ፈረስማይ ደረጃዉን የጠበቀ አስፓልት ከሶሰት አመት በፊት ይሰራል ተብሎ የነበር
9. ከሽረ -እንዳባጉና  በተሰራ በ 3 ወሩ ፈራርሶ አሁን ለአገልግሎት የማይሆን
10. ከተከዜ -ማይጌባ  ደርጃዉን የጠበቀ መንገድ ይሰራል ተብሎ የቀር አሁን አፈር እየደለደሉ የተዉት
11. ከሸራሮ -ጸገዴ-ወልቃይት ይሰራል በሚል ከገበሬዉ ዉጭጭ ብለዉ በሬና ፍየሉን ከዎሰዱ በሁዋላ የተሰወሩ፡፡ ዘንድሮ በግርግሩ ምክንያት ለሁለተኛ ጊዜ በጥቀምት ወር የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል
12. ከሸራሮ -ሕንፃፅ  ደረጃዉን የጠበቀ አስፓልት ከ 15 አመት በፊት ታቅዶ ያልተሰራ
ድርጅታችን ህወሓት አትኩሮት ሊሰጠው የሚገባ ትልቅ ህዝዝባዊ ጥያቄ ነው !!

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ